ኢሳይያስ 32:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሕዝቤ ምድር ላይ፥ በደስታ ከተማ ባሉት በደስታ ቤቶች ሁሉ ላይ እሾህና ኩርንችት ይበቅልባቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለ ሕዝቤ ምድር፣ እሾኽና አሜከላ ስለ በቀለበት ምድር፣ ስለ ፈንጠዝያ ቤቶች ሁሉ፣ ስለዚህችም መፈንጫ ከተማ አልቅሱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእሾኽ ቊጥቋጦና ኲርንችት በሕዝቤ ምድር ላይ በቅሎአል፤ ሕዝቦች በደስታ ይኖሩባቸው ስለ ነበሩት ቤቶችና በደስታ ተሞልታ ስለ ነበረችው ስለዚህች ከተማ አልቅሱ! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሕዝቤ ምድር ላይ በእርሻቸውም ላይ እሾህና አሜከላ ይበቅላሉ፤ ደስታም ከቤታቸው ሁሉ ይጠፋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሕዝቤ ምድር ላይ፥ በደስታ ከተማ ባሉት በደስታ ቤቶች ሁሉ ላይ እሾህና ኵርንችት ይወጣባቸዋል፥ |
አንቺ ጩኸትና ፍጅት የሞላብሽ ከተማ፥ የፈንጠዚያ ከተማ ሆይ፥ በአንቺ ውስጥ የተገደሉት በሰይፍ የተገደሉ አይደሉምን፥ በሰልፍስ የሞቱ አይደሉም?
የተመሸገችው ከተማ ብቻዋን ሆነች፤ እንደ ምድረ በዳ ሆና የተተወች መኖሪያ ሆናለች፤ በዚያም ጥጃ ይሰማራል፥ በዚያም ይተኛል ቅርንጫፍዋንም ይበላል።
ከሩብ ጋሻ የወይን ቦታ አንድ የባዶስ መስፈሪያ ያህል የወይን ጭማቂ ብቻ ይገኛል፤ አንድ የቆሮስ መስፈሪያ ዘር ተዘርቶ አንድ የኢፍ መስፈሪያ እህል ብቻ ይሰጣል።
እኔም፤ “ጌታ ሆይ፤ ይህ የሚሆነው እስከ መቼ ነው?” አልሁት፤ እርሱም መልሶ እንዲህ አለኝ፤ “ከተሞች እስኪፈራርሱና፤ የሚኖሩባቸው እስኪያጡ፤ ቤቶችም ወና እስኪሆኑና፤ ምድርም ፈጽሞ ባድማ እስክትሆን ድረስ፤
ከሰይፍ ፊትና ከከበባት የአፈር ድልድል ለመከላከል ስለ ፈረሱ ስለዚህች ከተማ ቤቶች፥ ስለ ይሁዳም ነገሥታት ቤቶች የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላልና፦
የእስራኤል ኃጢአት የሆኑት የአዌን የኮረብታው መስገጃዎች ይፈርሳሉ፤ እሾኽና አሜከላ በመሠዊያዎቻቸው ላይ ይበቅላል፤ እነርሱም ተራሮችን፦ “ሸፍኑን!” ኮረብቶችንም፦ “ውደቁብን!” ይሉአቸዋል።
እነሆ፥ ከጥፋት ሸሽተው ቢሄዱ እንኳ ግብጽ ትሰበስባቸዋለች፥ ሜምፎስም ትቀብራቸዋለች፤ ሳማም የብራቸውን ጌጥ ይወርሰዋል፥ እሾኽም በድንኳኖቻቸው ውስጥ ይበቅላል።