ኢሳይያስ 3:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልጆችን መሪዎቻቸው አደርጋለሁ፤ ያልበሰሉ ሕፃናትም ይገዟቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ልጆችን መሪዎቻቸው አደርጋለሁ፤ ያልበሰሉ ሕፃናትም ይገዟቸዋል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ገና ታዳጊ የሆኑና በዕድሜ ያልጠኑ ልጆችንም መሪዎች አድርጎ ይሾምባቸዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእነርሱ ላይ አለቆቻቸው እንዲሆኑ ጐልማሶችን እሾምባቸዋለሁ፤ ዘባቾችም ይገዙአቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አለቆቻቸው እንዲሆኑ ብላቴኖችን አስነሣባቸዋለሁ፥ ሕፃናቶችም ይገዙአቸዋል። |
ኢዮአቄምም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሀያ አምስት ዓመት ጎልማሳ ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ፤ በአምላኩም በጌታ ፊት ክፉ አደረገ።
ጌታ እንዲህ ይላል፤ የጽዮን ሴቶች ኰርተዋል፤ ዐንገታቸውን እያሰገጉ፤ በዐይናቸውም እየጠቀሱ ይሄዳሉ፤ እየተቈነኑ በመራመድ፤ የእግራቸውን ዐልቦ ያቃጭላሉ።
በእርግጥ ከጌታ ቁጣ የተነሣ ከፊቱ አውጥቶ እስኪጥላቸው ድረስ ይህ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ላይ ሆነ፤ ሴዴቅያስም በባቢሎን ንጉሥ ላይ ዐመፀ።