ኢሳይያስ 29:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአርኤልም ላይ የሚዋጉ፥ እርሷንና ምሽግዋንም የሚወጉ የሚያስጨንቋትም፥ የአሕዛብ ሁሉ ብዛት እንደ ሕልምና፥ እንደ ሌሊት ራእይ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አርኤልን የሚወጋ የአሕዛብ ሁሉ መንጋ፣ በእርሷና በምሽጓ ላይ አደጋ የሚጥልና የሚከብባት፣ እንደ ሕልም በሌሊትም እንደሚታይ ራእይ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔር መሠዊያ የሆነችውን ከተማ ለማጥቃት የሚመጡ የመንግሥታት ሠራዊቶች ሁሉ ከነጦር መሣሪያዎቻቸው ይደመሰሳሉ፤ እንደ ሕልም ወይም በእንቅልፍ ልብ እንደሚታሰብ ነገር የተረሱ ይሆናሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአርኤልም ላይ የሚዋጉ፥ ኢየሩሳሌምንም የሚወጉ፥ በእርሻዋም ላይ የሚሰበሰቡ የሚያስጨንቋትም፥ የአሕዛብ ሁሉ ብልጽግና እንደሚያልም ሰው ሕልም ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአርኤልም ላይ የሚዋጉ፥ እርስዋንና ምሽግዋንም የሚወጉ የሚያስጨንቋትም፥ የአሕዛብ ሁሉ ብዛት እንደ ሕልምና እንደ ሌሊት ራእይ ይሆናል። |
እነሆ፥ መልካም ዜና የሚያመጣ፥ ሰላምንም የሚያሰማ ሰው እግር በተራሮች ላይ ነው! ይሁዳ ሆይ በዓሎችሽን አክብሪ፥ ስእለቶችሽን ክፈዪ፤ አጥፊው ፈጽሞ ተቆርጧልና፥ ከእንግዲህም ወዲህ በአንቺ በኩል አያልፍምና።