ኢሳይያስ 29:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን የጠላቶችሽ ብዛት እንደ ደቀቀ ትቢያ፥ የጨካኞችም ብዛት እንደሚያልፍ ገለባ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ብዙ ጠላቶችሽ እንደ ትቢያ ብናኝ፣ የጨካኞች መንጋ በነፋስ እንደሚነዳ ገለባ ይሆናሉ። ድንገት ሳይታሰብም፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሩሳሌም ሆይ! በአንቺ ላይ በጠላትነት የሚነሡ የጠላት ሠራዊት ሁሉ እንደ ትቢያ በነው ይጠፋሉ፤ እጅግ የሚያስፈሩ ሠራዊቶቻቸውም ሳይታሰቡ በድንገት በነፋስ እንደሚወሰድ ገለባ ይሆናሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን የኃጥአን ብልጽግና እንደ ደቀቀ ትቢያ፥ የጠላቶችሽም ብዛት ነፋስ እንደሚያመጣው ገለባ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን የጠላቶችሽ ብዛት እንደ ደቀቀ ትቢያ፥ የጨካኞችም ብዛት እንደሚያልፍ ገለባ ይሆናል። |
የጨካኞችም ቁጣ እስትንፋስ ቅጥርን እንደሚመታ ዐውሎ ነፋስ በሆነ ጊዜ፥ ለድሀው መጠጊያ፥ ለችግረኛው በጭንቁ ጊዜ መሸሸጊያ፥ ከውሽንፍር መጠለያ፥ ከሙቀትም ጥላ ሆነሃል።
ግብጻውያን ሰዎች እንጂ አምላክ አይደሉም፤ ፈረሶቻቸውም ሥጋ እንጂ መንፈስ አይደሉም፤ ጌታ እጁን በሚዘረጋ ጊዜ፥ ረጂው ይሰናከላል ተረጂውም ይወድቃል፥ ሁሉም በአንድ ላይ ይጠፋሉ።
እነሆ፥ እንደ ተሳለች እንደ አዲስ ባለ ጥርስ ማሄጃ አድርጌሃለሁ፤ ተራሮችንም ታሄዳለህ ታደቅቃቸውማለህ፥ ኮረብቶችንም እንደ ገለባ ታደርጋቸዋለህ።
በዚህ ምክንያት ክፉ ነገር ይመጣብሻል፥ በምዋርትሽም እንዴት እንደምታርቂው አታውቂም፤ ጉዳት ይወድቅብሻል ልታስወግጂውም አትችይም፤ የማታውቂያትም ጉስቁልና ድንገት ትመጣብሻለች።
እነርሱም፦ “ሰላምና ደኅንነት ነው” በሚሉ ጊዜ ምጥ እንደ ያዛት እርጉዝ ሴት ድንገተኛ ጥፋት በእነርሱ ላይ ይመጣባቸዋል፤ ከቶም አያመልጡም።