የሐዘኑ ጊዜ ካበቃ በኋላም፥ ዳዊት ልኮ ቤርሳቤህን ወደ ቤቱ አስመጣት፤ ሚስቱ ሆነች፤ ወንድ ልጅም ወለደችለት፤ ነገር ግን ዳዊት የሠራው ሥራ ጌታን አላስደሰተውም ነበር።
ኢሳይያስ 29:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምክራቸውን ጥልቅ አድርገው ከጌታ ለሚሰውሩ፥ ሥራቸውንም በጨለማ ውስጥ አድርገው፦ “ማን ያየናል? ወይስ ማን ያውቀናል?” ለሚሉ ወዮላቸው! አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሐሳባቸውን ከእግዚአብሔር ለመደበቅ፣ ወደ ጥልቅ ጕድጓድ ለሚወርዱ ሥራቸውንም በጨለማ ለሚያከናውኑ፣ “ማን ያየናል? ማንስ ያውቅብናል” ለሚሉ ወዮላቸው! አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዕቅዳቸውን ከእግዚአብሔር ለመደበቅ ወደ ጥልቅ ቦታ ለሚሄዱ በጨለማ የሠሩትንም ሥራ “ማን ያይብናል? ማን ያውቅብናል?” ለሚሉ ሰዎች ወዮላቸው! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምክራቸውን ጥልቅ አድርገው ከእግዚአብሔር ለሚሰውሩ ወዮላቸው! ሥራቸውንም በጨለማ ውስጥ አድርገው፥ “ማን ያየናል? ወይስ ማን ያውቀናል?” ለሚሉ ወዮላቸው! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምክራቸውን ጥልቅ አድርገው ከእግዚአብሔር ለሚሰውሩ፥ ሥራቸውንም በጨለማ ውስጥ አድርገው፦ ማን ያየናል? ወይስ ማን ያውቀናል? ለሚሉ ወዮላቸው! |
የሐዘኑ ጊዜ ካበቃ በኋላም፥ ዳዊት ልኮ ቤርሳቤህን ወደ ቤቱ አስመጣት፤ ሚስቱ ሆነች፤ ወንድ ልጅም ወለደችለት፤ ነገር ግን ዳዊት የሠራው ሥራ ጌታን አላስደሰተውም ነበር።
እስራኤላውያን አምላካቸው እግዚአብሔር የሚጠላውን ነገር ሁሉ አደረጉ፤ ከዘብ ጠባቂዎች ማማ አንሥቶ እስከ ትልቅ ከተማ ድረስ በገጠር ከተሞቻቸው ሁሉ በየኰረብታዎቹ የአሕዛብ ማምለኪያ ስፍራዎችን ሠሩ፤
እናንተም፦ “ከሞት ጋር ቃል ኪዳን አድርገናል፥ ከሲኦልም ጋር ተማምለናል፤ ሐሰትን መሸሸጊያችን አድርገናልና፥ በሐሰትም ተሰውረናልና የሚትረፈረፍ መቅሠፍት ባለፈ ጊዜ አይደርስብንም” ስላላችሁ፥
ለዓመፀኞች ልጆች ወዮላቸው! ይላል ጌታ፤ ከእኔ ዘንድ ያልሆነን ምክር ይመክራሉ፥ ኃጢአትንም በኃጢአት ላይ ለመጨመር ከመንፈሴ ያልሆነውን ቃል ኪዳን ያደርጋሉ።
በክፋትሽ ታምነሻል፤ “የሚያየኝ የለም” ብለሻል፤ ጥበብሽና እውቀትሽ አታልለውሻል፥ በልብሽም፦ “እኔ ነኝ ከእኔም በቀር ሌላ የለም” ብለሻል።
እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ የእስራኤል ቤት ሽማግሌዎች እያንዳንዱ በስዕሉ ቤት በጨለማ የሚያደርጉትን አይተሃልን? እነርሱም፦ “ጌታ አያየንም፥ ጌታ ምድሪቱን ትቶአታል፥ ብለዋልና።”
እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ኃጢአት እጅግ በዝቶአል፥ ምድሪቱ በደም ተሞልታለች፥ ከተማይቱም ዓመፅን ተሞልታለች፥ ጌታ ምድሪቱን ትቶአታል፥ ጌታ አያይም ብለዋልና።
በዚያም ዘመን ኢየሩሳሌምን በመብራት እፈትሻለሁ፤ በአተላቸውም ላይ የሚረጉትን፥ በልባቸውም፦ “ጌታ መልካምም ክፉም አያደርግም” የሚሉትን ሰዎች እቀጣለሁ።
በቃላችሁ ጌታን አሰልችታችሁታል። እናንተም፦ እርሱን ያሰለቸነው በምንድን ነው? ትላላችሁ። “ክፉን የሚያደርግ ሁሉ በጌታ ፊት መልካም ነው፥ እርሱም በእነርሱ ደስ ይለዋል” ወይም “የፍትሕ አምላክ የት አለ?” በማለታችሁ ነው።
ስለዚህም፥ በጨለማ የተሰወረውን ወደ ብርሃን የሚያወጣ ደግሞም የልብን ምክር የሚገልጥ ጌታ እስኪመጣ ድረስ፥ ጊዜው ሳይደርስ አንዳች አትፍረዱ፤ በዚያን ጊዜም እያንዳንዱ ምስጋናው ከእግዚአብሔር ዘንድ ይሆናል።
የሚያሳፍረውን ስውር ነገር ጥለናል፤ በተንኮል አንመላለስም ወይም የእግዚአብሔርን ቃል በውሸት አንቀላቅልም፤ እውነትን በመግለጥ ግን በእግዚአብሔር ፊት ለሰው ሕሊና ሁሉ ራሳችንን እናቀርባለን።
ልጆችዋንም በሞት እገድላቸዋለሁ፤ አብያተ ክርስቲያናትም ሁሉ፥ ኩላሊትንና ልብን የምመረምር እኔ እንደሆንሁ ያውቃሉ፤ ለእያንዳንዳችሁም እንደ ሥራችሁ እሰጣችኋለሁ።