ኢሳይያስ 29:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ የሚደብት የእንቅልፍ መንፈስ አፍስሶባችኋል፤ ዐይኖቻችሁን፥ ነቢያትንም ጨፍኖባችኋል፤ ራሶቻችሁን ባለ ራእዮችን ሸፍኖባችኋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ከባድ እንቅልፍ ጥሎባችኋል፤ ዐይኖቻችሁን፣ ነቢያትን ጨፍኖባችኋል፤ ራሶቻችሁን፣ ባለራእዮችን ሸፍኖባችኋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ከባድ እንቅልፍ ስለ ጣለባችሁ እናንተ ነቢያት ዐይኖቻችሁን ጨፍናችኋል፤ እናንተም ባለ ራእዮች አእምሮአችሁን ዘግታችኋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር የእንቅልፍ መንፈስን አፍስሶባቸዋል፤ ዐይኖቻቸውን፥ የነቢያትንም ዐይን፥ የተሰወረውንም የሚያዩ የአለቆቻቸውን ዐይን ጨፍኖባቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር የእንቅልፍ መንፈስ አፍስሶባችኋል ዓይኖቻችሁን ነቢያትንም ጨፍኖባችኋል ራሶቻችሁን ባለ ራእዮችን ሸፍኖባችኋል። |
ስለዚህ፥ እነሆ፥ ድንቅ ነገርን በዚህ ሕዝብ መካከል፥ አስደማሚ ነገርን ተአምራትንም እንደገና አደርጋለሁ፤ የጥበበኞችም ጥበብ ትጠፋለች፥ የአስተዋዮችም ማስተዋል ትሰወራለች።
ነቢዩ ቢታለል፥ ቃልንም ቢናገር፥ ያንን ነቢይ ያታለልሁ እኔ ጌታ ነኝ፥ በእርሱም ላይ እጄን እዘረጋለሁ፥ ከሕዝቤ ከእስራኤል መካከልም አጠፋዋለሁ።
ስለዚህ ለእናንተ ራእይ የሌለው ሌሊት ይሆንባችኋል፥ የማትጠነቁሉበት ጨለማ ይሆንባችኋል፤ ፀሐይ በነቢያት ላይ ትጠልቅባቸዋለች፥ ቀኑም ይጨልምባቸዋል።
ይህም “ዐይኖቻቸው እንዳያዩ፥ ጆሮቻቸውም እንዳይሰሙ፥ እግዚአብሔር ከባድ የእንቅልፍን መንፈስ እስከ ዛሬ ድረስ ሰጣቸው፤” ተብሎ ተጽፎአል።
እንደ እነርሱ ከሆነ የማያምኑ ሰዎችን ልቦና፥ የእግዚአብሔር ምሳሌ የሆነ የክርስቶስ የክብሩ ወንጌል ብርሃን እንዳያበራላቸው፥ የዚህ ዓለም አምላክ አሳውሯል።
ስለዚህ ዳዊት በሳኦል ራስጌ አጠገብ የነበረውን ጦርና የውሃውን መያዣ ወሰደ፤ ከዚያም ሄዱ፤ ይህን ያየም ሆነ ያወቀ ወይም የነቃ ማንም አልነበረም። ከእግዚአብሔር ዘንድ ከባድ እንቅልፍ ስለ ወደቀባቸው ሁሉም ተኝተው ነበርና።
ቀደም ሲል በእስራኤል ዘንድ አንድ ሰው እግዚአብሔርን ለመጠየቅ ሲሄድ፥ “ኑ፥ ወደ ባለ ራእዩ እንሂድ” ይል ነበር፤ ዛሬ ነቢይ የሚባለው በዚያ ጊዜ ባለ ራእይ ይባል ነበርና።