ኢሳይያስ 29:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 ይህ ሁሉ ራእይ እንደ ታተመ የመጽሐፍ ቃል ሆኖባችኋል፤ ማንበብንም ለሚያውቅ፦ “ይህን አንብብ” ብለው ባዘዙት ጊዜ እርሱ፦ “ታሽጓልና አልችልም” ይላቸዋል፤ Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም11 ይህ ሁሉ ራእይ በጥቅልል መጽሐፍ ውስጥ እንደ ታሸገ ቃል ሆኖባችኋል። ጥቅልሉንም መጽሐፍ ማንበብ ለሚችል ሰው፣ “እባክህ አንብብልን” ብላችሁ ብትሰጡት፣ “ታሽጓልና አልችልም” ይላችኋል። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 የትንቢት ራእይ ሁሉ ትርጒም ከእናንተ ተሰውሮ እንደ ታሸገ መጽሐፍ ይሆናል፤ ወደሚያነብ ሰው ወስዳችሁ “አንብብልን” ብላችሁ ብትጠይቁት እንኳ “ስለ ታሸገ ላነበው አልችልም” ይላችኋል። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 ይህም ሁሉ ነገር እንደ ታተመ መጽሐፍ ቃል ሆኖባቸዋል፤ ማንበብንም ለሚያውቅ፥ “ይህን አንብብ” ብለው በሰጡት ጊዜ እርሱ፥ “ታትሟልና ማንበብ አልችልም” ይላቸዋል፤ Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 ራእዩም ሁሉ እንደ ታተመ መጽሐፍ ቃል ሆኖባችኋል፥ ማንበብንም ለሚያውቅ፦ ይህን አንብብ ብለው በሰጡት ጊዜ እርሱ፦ ታትሞአልና አልችልም ይላቸዋል፥ Ver Capítulo |