ለኢሳይያስም እንዲነግሩት የላከው መልእክት ከዚህ የሚከተለው ነው፦ “ዛሬ የታላቅ መከራ ቀን ነው፤ የሚያሳፍር ቅጣትና ውርደት እየደረሰብን ነው፤ የምትወልድበት ጊዜ ደርሶ ለማማጥ አቅም እንዳነሣት ሴት ሆነናል፤
ኢሳይያስ 26:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኛ ፀንሰናል ምጥም ይዞናል፥ ነፋስንም እንደምንወልድ ሆነናል፤ በምድርም ደኅንነት አላመጣንም፤ በዓለም እንዲኖሩም ሕዝብ አልወለድንም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አረገዝን በምጥም ተጨነቅን፤ ነገር ግን ነፋስን ወለድን፤ ለምድርም ድነትን አላመጣንም፤ የዓለምን ሕዝብ አልወለድንም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዳረገዙ ሴቶች ሆንን፤ ምጥም ይዞን ነበር፤ ነገር ግን ምንም ልጅ አልወለድንም፤ ለምድራችንም ድል አላስገኘንላትም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተን በመፍራት አቤቱ፥ እኛ ፀንሰናል፤ ምጥም ይዞናል፤ በምድርም የማዳንህን መንፈስ ወለድን፤ በዓለምም የሚኖሩ ይወድቃሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኛ ፀንሰናል ምጥም ይዞናል፥ ነፋስንም እንደምንወልድ ሆነናል፥ በምድርም ደኅንነት አላደረግነም፥ በዓለምም የሚኖሩ ይወድቃሉ። |
ለኢሳይያስም እንዲነግሩት የላከው መልእክት ከዚህ የሚከተለው ነው፦ “ዛሬ የታላቅ መከራ ቀን ነው፤ የሚያሳፍር ቅጣትና ውርደት እየደረሰብን ነው፤ የምትወልድበት ጊዜ ደርሶ ለማማጥ አቅም እንዳነሣት ሴት ሆነናል፤
አቤቱ፥ ከሰዎች፥ እድል ፈንታቸው በሕይወታቸው ከሆነች ከዚህ ዓለም ሰዎች በእጅህ አድነኝ፥ ከሰወርኸው መዝገብህ ሆዳቸውን አጠገብህ፥ ልጆቻቸው ተትረፍርፎላቸዋል የተረፋቸውንም ለሕፃናቶቻቸው ያተርፋሉ።
እነርሱም፦ “ሕዝቅያስ እንዲህ ይላል፦ ይህ ቀን የመከራና የተግሣጽ የዘለፋም ቀን ነው፤ ልጆች የሚወለዱበት ጊዜ ደርሶአል ለመውለድም ብርታቱ የለም።
ሕዝቡ ግን ሳኦልን፥ “ለእስራኤል ይህን ታላቅ ድል ያስገኘ ዮናታን መሞት ይገባዋልን? ይህ አይሆንም! ዛሬ ይህን ያደረገው በእግዚአብሔር ርዳታ ስለ ሆነ፥ ሕያው ጌታን! ከራስ ጠጉሩ አንዲቱ እንኳ መሬት ላይ አትወድቅም” አሉት። ስለዚህ ሰዎቹ ዮናታንን ታደጉት፤ እርሱም ከመሞት ዳነ።