ኢሳይያስ 22:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምርጦቹም ሸለቆችሽ ሠረገሎች ሞሉባቸው፤ ፈረሰኞችም በሮች ላይ ቆመዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መልካሞቹ ሸለቆዎችሽ በሠረገሎች ተሞልተዋል፤ ፈረሰኞችም በከተማዪቱ በሮች ላይ ቆመዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የይሁዳ ለምለም ሸለቆዎች በሠረገሎች የተሞሉ ሆነዋል። ፈረሰኞች በኢየሩሳሌም ቅጽር በር ፊት ለፊት ቆመዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መልካሞቹን ሸለቆችሽንም ሰረገሎች ሞሉባቸው፤ ፈረሰኞችም መቆሚያቸውን በበሮችሽ ላይ አደረጉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መልካሞቹንም ሸለቆችሽን ሰረገሎች ሞሉባቸው፥ ፈረሰኞችም መቆሚያቸውን በበር ላይ አደረጉ። |
እነሆ፥ እኔ በሰሜን ያሉትን የመንግሥታትን ወገኖች ሁሉ እጠራለሁ፥ ይላል ጌታ፤ እነርሱም ይመጣሉ እያንዳንዳቸውም በኢየሩሳሌም በር መግቢያ በዙሪያዋም ባለ ቅጥርዋ ሁሉ ላይ በይሁዳም ከተሞች ሁሉ ላይ ዙፋናቸውን ያስቀምጣሉ።
የብረት ምጣድም ውሰድ፥ በአንተና በከተማይቱ መካከል የብረት ቅጥር አድርገው፥ ፊትህንም ወደ እርሷ አቅና፥ የተከበበችም ትሆናለች፥ አንተም ትከብባታለህ። ይህም ለእስራኤል ቤት ምልክት ይሆናል።