እናንተ የጊልቦዓ ተራሮች ሆይ፤ በዚያ የኀያሉ ሰው ጋሻ ረክሶአልና፤ የሳኦል ጋሻ በዘይት መወልወሉ ቀርቶአልና፤ ጠልም ሆነ ዝናብ አይውረድባችሁ፤ የቁርባን እህል የሚያበቅሉም እርሻዎች አይኑራችሁ።
ኢሳይያስ 21:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማዕዱን ያዘጋጃሉ፥ ምንጣፉንም ይዘረጋሉ፥ ይበላሉም፥ ይጠጣሉም፤ እናንተ መሳፍንት ሆይ፥ ተነሡ፥ ጋሻውን አዘጋጁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማእዱን አሰናዱ፤ ምንጣፉን አነጠፉ፤ በሉ፤ ጠጡ! እናንተ ሹማምት ተነሡ፤ ጋሻውን በዘይት ወልውሉ! አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባየሁትም ራእይ ግብዣ ተዘጋጅቶ ለእንግዶች መቀመጫ ስጋጃዎች ተነጥፈዋል፤ እነርሱም ገና በመብላትና በመጠጣት ላይ ሳሉ፥ “እናንተ የጦር መኰንኖች! ጋሻችሁን ወልውላችሁ አዘጋጁ!” የሚል ድንገተኛ ትእዛዝ ተላለፈላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ማዕዱን አዘጋጁ፤ ብሉ፤ ጠጡ፤ እናንተ አለቆች ሆይ፥ ተነሡ፤ ጋሻውንም አዘጋጁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማዕዱን ያዘጋጃሉ፥ ምንጣፉንም ይዘረጋሉ፥ ይበሉማል፥ ይጠጡማል፥ እናንተ መሳፍንት ሆይ፥ ተነሡ፥ ጋሻውን አዘጋጁ። |
እናንተ የጊልቦዓ ተራሮች ሆይ፤ በዚያ የኀያሉ ሰው ጋሻ ረክሶአልና፤ የሳኦል ጋሻ በዘይት መወልወሉ ቀርቶአልና፤ ጠልም ሆነ ዝናብ አይውረድባችሁ፤ የቁርባን እህል የሚያበቅሉም እርሻዎች አይኑራችሁ።
ፍላጾችን ሳሉ ጋሻዎችንም አንሡ፤ ጌታ ሊያጠፋት አሳቡ በባቢሎን ላይ ነውና የሜዶንን ነገሥታት መንፈስ አስነሥቶአል፤ የጌታ በቀል ስለ መቅደሱ ሲል የሚበቀለው በቀል በእርሷ ላይ ነውና።
አለቆችዋንና ጥበበኞችዋንም፥ ገዢዎችዋንና ሹማምቶችዋን ኃያላኖችዋንም አሰክራለሁ፥ ለዘለዓለምም አንቀላፍተው አይነቁም፥ ይላል ስሙ የሠራዊት ጌታ የተባለው ንጉሥ።