ኢሳይያስ 21:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ አረብ የተነገረ ሸክም። የድዳናውያን ነጋዴዎች ሆይ፥ በዓረብ ዱር ወስጥ ታድራላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለ ዐረብ አገር የተነገረ ንግር፤ እናንተ በዐረብ ዱር የምትሰፍሩ፣ የድዳን ሲራራ ነጋዴዎች፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለ ዐረብ አገር የተነገረውም ቃል ይህ ነው፤ ከጭነት ግመሎቻችሁ ጋር በዐረብ በረሓ የምትሰፍሩ እናንተ የደዳን ሕዝብ ሆይ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሌሊትም በዲዳናውያን ጎዳና በዛፎች ውስጥ ታድራለህ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ ዓረብ የተነገረ ሸክም። የድዳናውያን ነጋዴዎች ሆይ፥ በዓረብ ዱር ወስጥ ታድራላችሁ። |
ይህም ሁሉ ነጋዴዎች ከሚከፍሉት ቀረጥ፥ ከንግድ ከሚገኘው ትርፍ፥ እንዲሁም ከዐረብ ነገሥታትና ከእስራኤል ክፍላተ ሀገር አስተዳዳሪዎች ከሚገባለት ግብር ጋር ተጨማሪ ነበር።
የዔሳውን ጥፋት እርሱን በምጐበኝበት ጊዜ አመጣበታለሁና፥ እናንተ በድዳን የምትኖሩ ሆይ! ሽሹ፥ ወደ ኋላ ተመለሱ፥ በጥልቅም ውስጥ ተቀመጡ።