ርብቃም ይስሐቅን አለችው፦ “ከኬጢ ሴቶች ልጆች የተነሣ ሕይወቴን ጠላሁት፥ ያዕቆብ ከዚህ አገር ሴቶች ልጆች ሚስትን የሚያገባ ከሆነ በሕይወት መኖር ለምኔ ነው?”
ኢሳይያስ 15:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሐሴቦንና ኤልያሊ ጮሁ፥ ድምፃቸው እስከ ያሀፅ ድረስ ተሰማ፤ ስለዚህ የሞዓብ ሰልፈኞች ጮኹ፤ ነፍሱም ራደች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሐሴቦንና ኤልያሊ ጮኹ፤ ድምፃቸው እስከ ያሀጽ ድረስ ተሰማ፤ ስለዚህ የሞዓብ ጦረኞች ጮኹ፤ ልባቸውም ራደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሐሴቦንና የኤልዓሌ ሕዝቦች ይጮኻሉ፤ የጩኸታቸውም ድምፅ እስከ ያሐጽ ድረስ ይሰማል፥ የሞአብ ወታደሮች ሳይቀሩ ወኔያቸው ከድቶአቸው በፍርሃት ተርበደበዱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሐሴቦንና ኤልያሊ ጮኹ፤ ድምፃቸውም እስከ ያሳ ድረስ ይሰማል፤ ስለዚህ የሞዓብ ወገብ ይታመማል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሐሴቦንና ኤልያሊ ጮሁ ድምፃቸው እስከ ያሀፅ ድረስ ይሰማል፥ ስለዚህ የሞዓብ ሰልፈኞች ጮኹ፥ ነፍስዋ በውስጥዋ ተንቀጠቀጠች። |
ርብቃም ይስሐቅን አለችው፦ “ከኬጢ ሴቶች ልጆች የተነሣ ሕይወቴን ጠላሁት፥ ያዕቆብ ከዚህ አገር ሴቶች ልጆች ሚስትን የሚያገባ ከሆነ በሕይወት መኖር ለምኔ ነው?”
ኤልያስ አንድ ቀን ሙሉ በበረሓ ተጓዘ፤ ከዚህ በኋላ ጉዞውን ቆም አድርጎ፥ በአንድ የክትክታ ዛፍ ጥላ ሥር ተቀመጠ፤ ሞቱንም በመመኘት “ጌታ ሆይ! አሁንስ ይብቃኝ፤ ከቀድሞ አባቶቼ አልበልጥምና ነፍሴን ውሰድ!” ሲል ጸለየ።
ከሐሴቦን ጮኹ እስከ ኤልያሊና እስከ ያሀጽ ድረስ ድምፃቸውን አሰሙ፤ ከዞዓር እስከ ሖሮናይምና እስከ ዔግላት ሺሊሺያ ድረስ ደርሶአል፤ የኔምሬም ውኃ ደግሞ ይደርቃል።
ፀሐይም በወጣ ጊዜ እግዚአብሔር የሚያቃጥል የምሥራቅ ነፋስ አዘጋጀ፥ ዮናስ ራሱን እስኪስት ድረስ ፀሐይ ራሱን መታው፤ ለነፍሱም ሞትን ለመነና “ከሕይወት ሞት ይሻላል” አለ።
ሴዎንም እስራኤል በምድሩ ላይ እንዳያልፍ ከለከለ፤ ሴዎንም ሕዝቡን ሁሉ ሰበሰበ፥ እስራኤልንም ለመውጋት ወደ ምድረ በዳ ወጣ፥ ወደ ያሀጽም መጣ፥ ከእስራኤልም ጋር ተዋጋ።