ኢሳይያስ 14:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአሕዛብ ነገሥታት ሁሉ በየቤታቸው በክብር አንቀላፍተዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአሕዛብ ነገሥታት ሁሉ በክብር አንቀላፍተዋል፤ በየመቃብራቸው ዐርፈዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገሥታት ሲሞቱ በክብር ይቀበራሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የአሕዛብ ነገሥታት ሁሉ በየቤታቸው በክብር አንቀላፍተዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአሕዛብ ነገሥታት ሁሉ በየቤታቸው በክብር አንቀላፍተዋል። |
እርሱንም ትተውት በሄዱ ጊዜ በጽኑ አቊስለውት ነበር፤ የገዛ ባርያዎቹም የካህኑ የዮዳሄን ልጅ ደም ለመበቀል ሲሉ አሴሩበት፥ በአልጋውም ላይ ገደሉት፥ ሞተም፤ በዳዊት ከተማ እንጂ በነገሥታት መቃብር አልቀበሩትም።
ከፍ ያለውን ደግሞ ሲፈሩ፥ ድንጋጤም በመንገድ ላይ ሲሆን፥ ለውዝም ሲያብብ፥ አንበጣም እንደ ሸክም ሲከብድ፥ ፈቃድም ሲጠፋ፥ ሰው ወደ ዘለዓለም ቤት ሲሄድ፥ አልቃሾችም በአደባባይ ሲዞሩ፥
ሰው መቶ ልጆች ቢወልድ፥ እጅግ ዘመንም በሕይወት ቢኖር፥ ዕድሜውም እጅግ ዓመት ቢሆን፥ ነገር ግን ነፍሱ መልካምን ነገር ባትጠግብ፥ መቃብርንም ባያገኝ፥ ከእርሱ ይልቅ ጭንጋፍ ይሻላል አልሁ።
አንተ ግን እንደ ተጠላ ቅርንጫፍ ከመቃብርህ ተጥለሃል፤ በሰይፍም የተወጉት፥ ተገድለውም ወደ ጉድጓዱ ድንጋዮች የወረዱ ከድነውሃል፤ እንደተረገጠም ሬሳ ሆነሃል።
መቃብር በዚህ ያስወቀርህ፥ ከፍ ባለው ሥፍራ መቃብር ያሠራህ፥ በድንጋይም ውስጥ ለራስህ መኖሪያ ያሳነጽክ በዚህ ስፍራ ምን መብት አለህ? በዚህስ ለአንተ ወገን የሆነ ማን አለ?