ኢሳይያስ 13:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተኩላዎችም በግንቦቻቸው፥ ቀበሮዎችም በተዋቡ ቤተ መንግሥቶቿ ይጮኻሉ፤ ጊዜዋ ቀርቦአል፤ ቀኗም አይራዘምም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጅቦች በምሽጎቿ፣ ቀበሮዎችም በተዋቡ ቤተ መንግሥቶቿ ይጮኻሉ፤ ጊዜዋ ቀርቧል፤ ቀኗም አይራዘምም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በታላላቅ ሕንጻዎችዋና በቤተ መንግሥትዋ ውስጥ የጅቦችና የተኲላዎች ጩኸት ያስተጋባል፤ እነሆ በዚህ ዐይነት ባቢሎን የምትጠፋበት ጊዜ ደርሶአል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተኵላዎችም በዚያ ያድራሉ፤ ቀበሮዎችም በሚያማምሩ አዳራሾቻቸው ይዋለዳሉ፤ ይህም ሁሉ ፈጥኖ ይሆናል፤ አይዘገይምም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ተኵላዎችም በግንቦቻቸው፥ ቀበሮዎችም በሚያማምሩ አዳራሾቻቸው ይጮኻሉ፥ ጊዜዋም ለመምጣት ቀርቦአል ቀንዋም አይዘገይም። |
ከተማይቱን የድንጋይ ክምር፥ የተመሸገችውን ከተማ ውድማ እንድትሆን፥ የኀጥኣንንም አዳራሽ ከተማ እንዳትሆን አድርገሃል፤ ደግማም አትገነባም።
አዳራሹ ወና ይሆናል፥ በሰው የተጨናነቀውም ከተማ ወና ይሆናል፤ ምሽጉና ግንቡም ለዘለዓለም ዋሻ፥ የምድረ በዳም አህያ ደስታ፥ የመንጎችም ማሰማርያ ይሆናል።
የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላልና፦ “የባቢሎን ሴት ልጅ በመረገጥ ላይ እንዳለ ዐውድማ ነች፤ ጥቂት ቈይታ የመከር ጊዜ ይደርስባታል።”
በዚህ ምክንያት አለቅሳለሁ፥ ዋይ ዋይ እላለሁ፥ ባዶ እግሬንና ራቁቴን እሄዳለሁ፤ እንደ ቀበሮ አላዝናለሁ፥ እንደ ሰጎን ልጆችም የዋይታ ድምፅ አሰማለሁ።
መንጎችም የምድርም አራዊት ሁሉ በውስጧ ይኖራሉ፥ ጉጉትና ጃርት በዓምዶችዋ መካከል ያድራሉ፥ ድምፅም በመስኮት ይጮኻል፥ በመድረኩ ላይ ጥፋት ይደርሳል የዝግባ እንጨት ሥራ ይገለጣልና።
ለገንዘብ ከመስገብገባቸው የተነሣ ራሳቸው ያዘጋጁትን ታሪክ እያወሩ ይበዘብዙአችኋል። ፍርዳቸውም ከብዙ ዘመን በፊት ጀምሮ ተዘጋጅቶላቸዋል፤ ጥፋትም በእርግጥ ይጠብቃቸዋል!