ኢሳይያስ 13:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የመንግሥታት ዕንቁ፤ የከለዳውያን ትምክሕት፤ የሆነችውን ባቢሎንን፤ እግዚአብሔር እንደ ሰዶምና እንደ ገሞራ ይገለብጣታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የመንግሥታት ዕንቍ፣ የከለዳውያን ትምክሕት የሆነችውን ባቢሎንን፣ እግዚአብሔር እንደ ሰዶምና እንደ ገሞራ ይገለብጣታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የባቢሎን መንግሥት ከመንግሥታት ሁሉ እጅግ የተዋበች ናት፤ ለሕዝብዋም መመኪያ ናት፤ ነገር ግን እኔ እግዚአብሔር ባቢሎንን እንደ ሰዶምና እንደ ገሞራ እገለብጣታለሁ! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የመንግሥታት ክብር፥ የከለዳውያንም የትዕቢታቸው ትምክሕት የሆነች ባቢሎንም እግዚአብሔር እንደ ገለበጣቸው እንደ ሰዶምና እንደ ገሞራ ትሆናለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ሰዶምንና ገሞራን ባፈረሰ ጊዜ እንደ ነበረው፥ የመንግሥታት ክብር የከለዳውያንም ትዕቢት ጌጥ ባቢሎን እንዲሁ ትሆናለች። |
እነሆም፥ በፈረሶች የሚቀመጡ፥ ሁለት ሁለት ሁነው የሚሄዱ ፈረሰኞች ይመጣሉ ብሎ ጮኸ፤ እርሱም መልሶ፦ ባቢሎን ወደቀች ወደቀች፥ የተቀረጹም የአማልክቶችዋ ምስሎች ሁሉ በምድር ላይ ተጥለው ደቀቁ አለ።
እናንተ ሁሉ፥ በአንድነት ተሰብስባችሁ ስሙ፤ ከእነርሱ ይህን የተናገረ ማን ነው? ጌታ የወደደው ፈቃዱን በባቢሎን ላይ ያደርጋል፥ ክንዱም በከለዳውያን ላይ ይሆናል።
ሰባው ዓመትም በተፈጸመ ጊዜ፥ የባቢሎንን ንጉሥና ያንን ሕዝብ ስለ ኃጢአታቸው እቀጣለሁ፥ ይላል ጌታ፥ የከለዳውያንንም ምድር ለዘለዓለም ባድማ አደርጋታለሁ።
ሰዶምና ገሞራ በእነርሱም አጠገብ የነበሩት ጎረቤቶቻቸው እንደ ተገለባበጡ፥ ይላል ጌታ፥ እንዲሁ ማንም ሰው በዚያ አይቀመጥም የሰው ልጅም አይኖርባትም።
ሰዶምንና ገሞራን በአጠገባቸውም የነበሩትን ጎረቤቶቻቸውን እግዚአብሔር እንደ ገለባበጣቸው፥ ይላል ጌታ፥ እንዲሁ ማንም ሰው በዚያ አይቀመጥም የሰው ልጅም አይኖርባትም።
እንዲህ በል፦ ‘አቤቱ፥ ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ ማንም እንዳይቀመጥባት፥ ለዘለዓለምም ባድማ እንድትሆን ልታጠፋት በዚህች ስፍራ ላይ አንተ ተናግረሃል።’
“ሰዶምንና ገሞራን እግዚአብሔር እንደ ገለባበጣቸው፥ እንዲሁ ገለባበጥኋችሁ፥ እናንተም ከእሳት ውስጥ እንደ ተነጠቀ ትንታግ ሆናችሁ፤ ነገር ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፥” ይላል ጌታ።
ስለዚህ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ እኔ ሕያው ነኝና ሞዓብ እንደ ሰዶም፥ የአሞንም ልጆች እንደ ገሞራ ይሆናሉ፥ አረም እንደ ዋጠው ስፍራና እንደ ጨው ጉድጓድ ለዘለዓለምም ይጠፋሉ፤ የሕዝቤም ትሩፍ ይበዘብዛቸዋል፥ ከወገኔም የተረፉት ይወርሱአቸዋል።
ደግሞም ኢሳይያስ “የሠራዊት ጌታ ዘር ባያስቀርልን ኖሮ፥ እንደ ሰዶም በሆንን ነበር፥ ገሞራንም በመሰልን ነበር” ብሎ አስቀድሞ እንደ ተናገረው ነው።
ምድርም በሁለንተናዋ ዲንና ጨው፥ ዐመድም እንደ ሆነች፥ እንዳይዘራባት፥ እንዳይበቅልባትም፥ ማናቸውም ሣር እንዳይወጣባት፥ ጌታ በታላቅ ቁጣና መዓቱ እንደ ገለባበጣቸው እንደ ሰዶምና ገሞራ፥ እንደ አዳማና ጺባዮ እንደ ሆነች ባዩ ጊዜ፥
በራሳቸውም ላይ ትቢያ ነስንሰው እያለቀሱና እያዘኑ “በባሕር መርከቦች ያሉአቸውን ሁሉ ከሀብቷ የተነሣ ሀብታም ላደረገች ለታላቂቱ ከተማ ወዮላት! ወዮላት! በአንድ ሰዓት ጠፍታለችና፤” እያሉ ጮኹ።