ኢሳይያስ 12:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከመድኀኒቴ ምንጮች ውሃ በደስታ ትቀዳላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከድነቴ ምንጮች ውሃ በደስታ ትቀዳላችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከደኅንነት ምንጭ ውሃ በደስታ ትቀዳላችሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ውኃውንም ከሕይወት ምንጮች በደስታ ትቀዳላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ውኃውንም ከመድኃኒት ምንጮች በደስታ ትቀዳላችሁ። |
በወናዎቹ ኮረብቶች ላይ ወንዞችን፥ በሸለቆዎችም መካከል ምንጮችን እከፍታለሁ፤ ምድረ በዳውን ለውኃ ማከማቻ፥ የጥማትንም ምድር ለውሃ መፍለቂያ አደርጋለሁ።
ሕዝቤ ሁለት ክፉ ነገሮችን ሠርቷል፤ እኔን የሕይወት ውኃ ምንጭን ትተውኛል፥ ውኃ መቋጠር የማይችሉ የተሸነቈሩ ጉድጓዶች ለራሳቸው ቆፍረዋል።
ወንዙ በሚገባበት ስፍራ ያለ ሕያው ነፍስ ያለው ተንቀሳቃሽ ሁሉ በሕይወት ይኖራል፤ ዓሣዎች እጅግ ይበዛሉ፤ ይህ ውኃ በዚያ ስለ ደረሰ የባሕሩ ውኃ ይፈወሳል፥ ወንዙ በሚገባበት ያለው ሁሉ በሕይወት ይኖራል።
በዙፋኑ መካከል ያለው በጉ እረኛቸው ይሆናልና፤ ወደ ሕይወትም ውሃ ምንጭ ይመራቸዋልና፤ እግዚአብሔርም እንባዎችን ሁሉ ከዐይናቸው ያብሳል።”
ሐናም እንዲህ ብላ ጸለየች፦ “ልቤ በጌታ ደስ ይለዋል፥ ቀንዴም በጌታ ከፍ ከፍ ብሏል፤ በማዳንህ ደስ ብሎኛልና፥ አፌ በጠላቶቼ ላይ ተከፈተ።