ሆሴዕ 7:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሴራቸው ልባቸው እንደ ምድጃ ተቃጥላለችና፤ ጋጋሪያቸው ሌሊቱን ሁሉ አንቀላፋ፤ በነጋም ጊዜ እንደ እሳት ነበልባል ነደደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልባቸው እንደ ምድጃ የጋለ ነው፤ በተንኰል ይቀርቡታል፤ ቍጣቸው ሌሊቱን ሙሉ ይጤሳል፤ እንደሚነድድም እሳት በማለዳ ይንበለበላል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሤራ ለመጐንጐን ልባቸው እንደ ምድጃ የጋለ ነው፤ ቊጣቸው ሌሊቱን ሙሉ ሲጤስ ያድራል፤ ሲነጋ ግን እንደሚነድ እሳት ይንበለበላል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እያደቡ ልባቸውን እንደ ምድጃ አዘጋጅተዋል፤ ጋጋሪያቸውም ሌሊቱን ሁሉ አንቀላፋ፤ በጠባም ጊዜ እንደ እሳት ነበልባል ይነድዳል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እያደቡ ልባቸውን እንደ ምድጃ አዘጋጅተዋል፥ አበዛቸውም ሌሊቱን ሁሉ አንቀላፋ፥ በጠባም ጊዜ እንደ እሳት ነበልባል ይነድዳል። |