ዕብራውያን 12:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያንጊዜ ድምፁ ምድርን አናወጧት ነበር፤ አሁን ግን “አንድ ጊዜ ደግሜ እኔ ሰማይን አናውጣለሁ እንጂ ምድርን ብቻ አይደለም፤” ብሎ ተስፋ ሰጥቶአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ጊዜ ድምፁ ያናወጠው ምድርን ነበር፤ አሁን ግን፣ “አንድ ጊዜ እንደ ገና ምድርን ብቻ ሳይሆን፣ ሰማያትንም አናውጣለሁ” ብሎ ቃል ገብቷል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ ቃሉ ምድርን አናውጦአል፤ አሁን ግን “ምድርን ብቻ ሳይሆን አንድ ጊዜ ደግሜ ሰማይን ጭምር አናውጣለሁ” በማለት ቃል ገብቶአል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያንጊዜ ቃል ምድርን አናወጣት፤ “አሁንም እኔ ምድርን እንደ ገና አንድ ጊዜ አናውጣታለሁ” ብሎ ተናገረ፤ ምድርን ብቻም አይደለም፤ ሰማይንም ጭምር እንጂ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ጊዜ ድምፁ ምድርን አናወጠ፥ አሁን ግን፦ አንድ ጊዜ ደግሜ እኔ ሰማይን አናውጣለሁ እንጂ ምድርን ብቻ አይደለም ብሎ ተስፋ ሰጥቶአል። |
ጌታም በጽዮን ሆኖ ድምፁን ከፍ አድርጎ ይጮኻል፥ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ቃሉን ያሰማል፥ ሰማይና ምድርም ይናወጣሉ፥ ጌታ ግን ለሕዝቡ መሸሸጊያ፥ ለእስራኤልም ልጆች መጠጊያ ይሆናል።
የመንግሥታትንም ዙፋን እገለብጣለሁ፥ የአሕዛብ መንግሥታትን ኃይል አጠፋለሁ፤ ሰረገሎችንና ነጂዎቻቸውን እገለብጣለሁ፤ ፈረሶችንና ፈረሰኞቻቸው እያንዳንዱ በወንድሙ ሰይፍ ይወድቃሉ።
አቤቱ፥ ከሴይር በወጣህ ጊዜ፥ ከኤዶምያስም ሜዳ በተራመድህ ጊዜ፥ ምድሪቱ ተናወጠች፥ ሰማያቱም አንጠበጠቡ፥ ደመናትም ደግሞ ውኃን አንጠበጠቡ።