ዕንባቆም 3:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቸነፈር በፊቱ ይሄዳል፥ መቅሠፍትም ከእግሩ ይወጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መቅሠፍት በፊቱ ሄደ፤ ቸነፈርም እግር በእግር ተከተለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቸነፈር ፊት ፊቱ ይሄዳል፤ መቅሠፍትም ከኋላው ይከተለዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቸነፈር በፊቱ ይሄዳል፥ የእሳትም ነበልባል ከእግሩ ይወጣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቸነፈር በፊቱ ይሄዳል፥ የእሳትም ነበልባል ከእግሩ ይወጣል። |
የቃል ኪዳኑንም በቀል የሚበቀል ሰይፍ አመጣባችኋለሁ፤ ወደ ከተሞቻችሁም ትሰበሰባላችሁ፥ በመካከላችሁም ቸነፈርን እልክባችኋለሁ፤ በጠላትም እጅ ተላልፋችሁ ትሰጣላችሁ።