ዕንባቆም 3:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ ሰምቻለሁ፥ አንጀቴ ራደብኝ፥ ከድምፁ የተነሣ ከንፈሮቼ ተንቀጠቀጡ፤ መበስበስ ወደ አጥንቶቼ ውስጥ ገባ፥ በውስጤም ተንቀጠቀጥሁ፥ በአስጨነቁን ሕዝብ ላይ እስኪመጣ ድረስ፥ የመከራን ቀን ዝም ብዬ እጠብቃለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔ ሰማሁ፤ ልቤም ደነገጠብኝ፤ ከንፈሬ ከድምፁ የተነሣ ተንቀጠቀጠ፤ ፍርሀት እስከ ዐጥንቴ ዘልቆ ገባ፤ እግሬም ተብረከረከ፤ ሆኖም በሚወርረን ሕዝብ ላይ እስኪመጣ ድረስ፣ የጥፋትን ቀን በትዕግሥት እጠባበቃለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን ሁሉ ስሰማ ሰውነቴ ይርበደበዳል፤ ድምፁም ከንፈሮቼን ያንቀጠቅጣል፤ አጥንቶቼ ይበሰብሳሉ፤ እግሮቼ ከታች ይብረከረካሉ፤ በጠላቶቻችን ላይ መከራ የሚደርስበትን ጊዜ በትዕግሥት እጠባበቃለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ ሰምቻለሁ፥ ልቤም ደነገጠብኝ፣ ከድምፁ የተነሣ ከንፈሮቼ ተንቀጠቀጡ፣ መንቀጥቀጥ ወደ አጥንቶቼ ውስጥ ገባ፣ በስፍራዬ ሆኜ ተናወጥሁ፣ በሚያስጨንቁን ሕዝብ ላይ እስኪመጣ ድረስ የመከራን ቀን ዝም ብዬ እጠብቃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ ሰምቻለሁ፥ ልቤም ደነገጠብኝ፥ ከድምፁ የተነሣ ከንፈሮቼ ተንቀጠቀጡ፥ መንቀጥቀጥ ወደ አጥንቶቼ ውስጥ ገባ፥ በስፍራዬ ሆኜ ተናወጥሁ፥ በሚያስጨንቁን ሕዝብ ላይ እስኪመጣ ድረስ የመከራን ቀን ዝም ብዬ እጠብቃለሁ። |
ስለ ነቢያት፤ ልቤ በውስጤ ተሰብሮአል አጥንቶቼም ሁሉ ታውከዋል፤ ከጌታ የተነሣ፥ ከቅዱስ ቃላቱም የተነሣ የወይን ጠጅ እንዳሸነፈው እንደ ሰካራም ሰው ሆኛለሁ።
አንጀቴ! አንጀቴ! ልቤ በጣም ታምሞአል፥ በውስጤም ልቤ ታውኮብኛል፤ ነፍሴ ሆይ! የመለከትን ድምፅና የጦርነትን ሁካታ ሰምተሻልና ዝም ማለት አልችልም።
የእስራኤል ቤት ሆይ! እነሆ፥ ሕዝብን ከሩቅ አመጣባችኋለሁ፥ ይላል ጌታ፤ ጽኑ ጥንታዊ ሕዝብ ነው፥ ቋንቋቸውንም የማታውቀው የሚናገሩትንም የማታስተውለው ሕዝብ ነው።
ሬስ። አቤቱ፥ ተጨንቄአለሁና፥ አንጀቴም ታውኮብኛልና ተመልከት፥ ዓመፃን ፈጽሞ አድርጌአለሁና ልቤ በውስጤ ተገላበጠብኝ፥ በሜዳ ሰይፍ ልጆቼን አጠፋ በቤትም ሞት አለ።
ጌታ ሆይ፥ ዝናህን ሰምቻለሁ፥ በሥራህም ጌታ ሆይ ፈራሁ፥ በዓመታት መካከል አድሰው፥ በዓመታት መካከል አስታውቀው፥ በቁጣ ጊዜ ምሕረትን አስብ።