La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዕንባቆም 1:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ክፉ ሥራ ለምን አሳየኸኝ? ድካምንስ ለምን ትመለከታለህ? ጥፋትና ግፍ በፊቴ ነው፤ ጠብና ክርክር ይነሣሉ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስለ ምን በደልን እንዳይ አደረግኸኝ? እንዴትስ ግፍ ሲፈጸም ትታገሣለህ? ጥፋትና ግፍ በፊቴ አለ፤ ጠብና ግጭት በዝቷል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ለምን ይህ ሁሉ ግፍ ሲደርስ እንዳይ አደረግኸኝ? አንተስ ይህ ሁሉ ግፍ ሲፈጸም እንዴት ዝም ብለህ ትመለከታለህ? ጥፋትንና ዐመፅን አያለሁ፤ ጠብና ክርክርም ይነሣሉ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በደልንስ ስለ ምን አሳየኸኝ? ጠማምነትንስ ስለ ምን ትመለከታለህ? ጥፋትና ግፍ በፊቴ ነው፣ ጠብና ክርክር ይነሣሉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በደልንስ ስለ ምን አሳየኸኝ? ጠማምነትንስ ስለ ምን ትመለከታለህ? ጥፋትና ግፍ በፊቴ ነው፥ ጠብና ክርክር ይነሣሉ።

Ver Capítulo



ዕንባቆም 1:3
16 Referencias Cruzadas  

እኔም ተመለስሁ፥ ከፀሐይ በታችም የሚደረገውን ግፍ ሁሉ አየሁ፥ እነሆም፥ የተገፉት ሰዎች እንባ፥ የሚያጽናናቸውም አልነበረም፥ በሚገፉአቸውም እጅ ኃይል ነበረ፥ እነርሱን ግን የሚያጽናናቸው አልነበረም።


በጠቅላላው ይህ ለአገሩ ይጠቅማል፤ ንጉሥም ከእርሻ ይጠቀማል።


እናንተ ከጽድቅ የራቃችሁ እልከኞች፥ ስሙኝ፤


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የወይን ቦታ የእስራኤል ቤት ነው፤ የይሁዳ ሰዎችም የደስታው አትክልት ናቸው። ፍትሕን ፈለገ፤ ነገር ግን ደም ማፍሰስን አየ፤ ጽድቅን ፈለገ፤ ነገር ግን የጭንቅን ጩኸት ሰማ።


እናቴ ሆይ፥ ወዮልኝ! ለምድር ሁሉ የሙግትና የጥል ሰው የሆንሁትን ወለድሽኝ፤ ለማንም አላበደርሁም፥ ማንም ለእኔ አላበደረም፥ ነገር ግን ሁሉ ይረግመኛል።


ድካምንና ጣርን እንዳይ፥ ዘመኔም በእፍረት እንድታልቅ ለምን ከማኅፀን ወጣሁ?


በተናገርሁ ቍጥር እጮኻለሁ፤ “ግፍና ጥፋት” ብዬ እጮኻለሁ፤ የጌታ ቃል ቀኑን ሁሉ ስድብና መዘበቻ ሆኖብኛልና።


አንተም የሰው ልጅ ሆይ፥ ኩርንችትና እሾህ ከአንተ ጋር ቢኖሩም፥ በጊንጦች መካከል ብትቀመጥም፥ አትፍራ፥ ቃላቸውንም አትፍራ፥ እነርሱ ዓመፀኛ ቤት ናቸውና ቃላቸውን አትፍራ፥ ፊታቸውንም አትፍራው።


“እነሆ እንደ በጎች በተኩላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ብልሆች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ።


ያ ጻድቅ ሰው፥ በመካከላቸው ሲኖር ዕለት ከዕለት የዐመፀኞችን ሴሰኛ ኑሮ እያየና እየሰማ በክፉ ሥራቸው ጻድቅ ነፍሱን ቢያስጨንቅም፤