ዘፍጥረት 7:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ኖኅን እንዲህ አለው፦ “በዚህ ዘመን ካለው ትውልድ መካከል ጻድቅ አንተ ሆነህ አይቼሃለሁና፥ አንተ ቤተሰቦችህን ሁሉ ይዘህ ወደ መርከብ ግባ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ኖኅን እንዲህ አለው፤ “በዚህ ትውልድ መካከል አንተን ጻድቅ ሆነህ አግኝቼሃለሁና ቤተ ሰብህን በሙሉ ይዘህ ወደ መርከቧ ግባ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ኖኅን እንዲህ አለው፤ “በዚህ ዘመን ካለው ትውልድ መካከል ጻድቅ አንተ ብቻ ሆነህ ስላገኘሁህ፥ ከመላው ቤተሰብህ ጋር ወደ መርከቡ ግባ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር አምላክም ኖኅን አለው፥ “አንተ ቤተሰቦችህን ሁሉ ይዘህ ወደ መርከብ ግባ፤ በዚህ ትውልድ በፊቴ ጻድቅ ሆነህ አይችሃለሁና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ኖኅን አለው፤ አንተ ቤተሰቦችህን ሁሉ ይዘህ ወደ መርከብ ግባ በዚህ ትውልድ በፊቴ ጻድቅ ሆነህ አይቼሃለሁና። |
እናንተ ፍርዱን የጠበቃችሁ፥ የምድር ትሑታን ሁሉ፥ ጌታን ፈልጉ፤ ጽድቅን ፈልጉ፥ ትሕትናን ፈልጉ፤ ምናልባት በጌታ ቁጣ ቀን ትሰወሩ ይሆናል።
ኖኅ ገና ስለማይታየው ነገር ተረድቶ እግዚአብሔርን እየፈራ ቤተ ስዎቹን ለማዳን መርከብን በእምነት አዘጋጀ፤ በዚህም ዓለምን ኰነነ፤ በእምነትም የሚገኘውን ጽድቅ ወራሽ ሆነ።
እነዚህ ቀድሞ በኖኅ ዘመን መርከብ ሲሠራ እግዚአብሔር በትዕግሥት ሲጠብቃቸው አንታዘዝም ያሉ ናቸው። በውሃ የዳኑት ጥቂት ሲሆኑ እነርሱም ስምንት ሰዎች ብቻ ነበሩ።