የአሴር እንጀራው ወፍራም ነው፥ ለነገሥታቱም ደስ የሚያሰኝ መብልን ይሰጣል።
“አሴር ማእደ ሰፊ ይሆናል፤ ለነገሥታትም የሚስማማ ምግብ ያቀርባል።
“አሴር ከምድሩ ብዙ ሀብት አግኝቶ ይበለጽጋል፤ በነገሥታት ፊት መቅረብ የሚችል ጥሩ ምግብ ያዘጋጃል።
“የአሴር እንጀራ ወፍራም ነው፤ እርሱም ለአለቆች ደስ የሚያሰኝ መብልን ይሰጣል።
የአሴር እንጀራው ወፍራም ነው ለነገሥታቱም ደስ የሚያሰኝ መብልን ይስጣል።
ልያም፦ ደስታ ሆነልኝ፥ ሴቶች ያመሰግኑኛልና አለች፥ ስሙንም አሴር ብላ ጠራችው።
የአሴር ልጆች፦ ይምና፥ ይሽዋ፥ ይሽዊና በሪዓ ናቸው። እኅታቸው ሤራሕ ትባላለች። የበሪዓ ልጆች ደግሞ ሔቤርና ማልኪኤል ናቸው።