ልያም፦ “እግዚአብሔር መልካም ስጦታን ሰጠኝ፥ እንግዲህስ ባሌ ከእኔ ጋር ይኖራል፥ ስድስት ልጆችን ወልጄለታለሁና” አለች፥ ስሙንም ዛብሎን ብላ ጠራችው።
ዘፍጥረት 49:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዛብሎን በባሕር ዳር ይቀመጣል፥ እርሱም ለመርከቦች ወደብ ይሆናል፥ ዳርቻውም እስከ ሲዶና ድረስ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ዛብሎን፣ በባሕር ዳር ይኖራል፤ የመርከቦች መጠጊያም ይሆናል፤ ወሰኑም እስከ ሲዶና ይደርሳል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ዛብሎን በባሕር ዳር ይኖራል፤ ወደቡም የመርከቦች ማረፊያ ይሆናል፤ የመኖሪያውም ወሰን እስከ ሲዶና ይደርሳል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ዛብሎን ጫማውን አዝቦ ይኖራል፤ እርሱም እንደ መርከቦች ወደብ ይሆናል፤ ዳርቻውም እስከ ሲዶና ይሰፋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዛብሎን በባሕር ዳር ይቀመጣል እርሱም ለመርከቦች ወደብ ይሆናል ዳርቻውም እስከ ሲዶን ድረስ ነው። |
ልያም፦ “እግዚአብሔር መልካም ስጦታን ሰጠኝ፥ እንግዲህስ ባሌ ከእኔ ጋር ይኖራል፥ ስድስት ልጆችን ወልጄለታለሁና” አለች፥ ስሙንም ዛብሎን ብላ ጠራችው።