በግብጽ ምድርና በከነዓን ምድር ብሩም በሸመታ አለቀ፥ የግብጽ ሰዎች ሁሉም ወደ ዮሴፍ እየመጡ፦ “የምንመገበው ስጠን፥ ስለምን በፊትህ እንሞታለን? ብሩ አልቆብናልና” አሉት።
ዘፍጥረት 47:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮሴፍም፦ “ከብቶቻችሁን አምጡልኝ፥ ብር ካለቀባችሁ በከብቶቻችሁ ፋንታ እህል እሰጣችኋለሁ” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮሴፍም፣ “ከብቶቻችሁን አምጡ፤ ገንዘባችሁ ካለቀ በከብቶቻችሁ ለውጥ እህል እሰጣችኋለሁ” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮሴፍም “ገንዘባችሁ ካለቀ ከብቶቻችሁን አምጡና በእነርሱ ለውጥ እህል እሰጣችኋለሁ” አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮሴፍም፥ “ከብቶቻችሁን አምጡልኝ፤ ብር ከአለቀባችሁ በከብቶቻችሁ ፈንታ እህል እሰጣችኋለሁ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮሴፍም፦ ከብቶቻችሁን አምጡልኝ ብር ካለቀባችሁ በከብቶቻችሁ ፋንታ እህል እሰጣችኍለሁ አለ። |
በግብጽ ምድርና በከነዓን ምድር ብሩም በሸመታ አለቀ፥ የግብጽ ሰዎች ሁሉም ወደ ዮሴፍ እየመጡ፦ “የምንመገበው ስጠን፥ ስለምን በፊትህ እንሞታለን? ብሩ አልቆብናልና” አሉት።
ከብቶቻቸውንም ወደ ዮሴፍ አመጡ፥ ዮሴፍም በፈረሶቻቸው በበጎቻቸውም በላሞቻቸውም በአህዮቻቸውም ፋንታ እህልን ሰጣቸው፥ ያንንም ዓመት በከብቶቻቸው ሁሉ ልዋጭ ህልን መገባቸው።
በቀረውስ ወንድሞች ሆይ! እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ክቡር የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ፥ ምስጉን የሆነውን ነገር ሁሉ፥ በጎነት ቢሆን ምስጋናም ቢሆን፥ እነዚህን አስቡ፤