ዘፍጥረት 46:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም በግ የሚጠብቁ ሰዎች ናቸው፥ እንስሳ ያረቡ ነበርና፥ በጎቻቸውንና ላሞቻቸውን ያላቸውንም ሁሉ አመጡ፥’ ብዬ እነግረዋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰዎቹ ከብት የሚጠብቁ ስለ ሆኑ እረኞች ናቸው፤ ሲመጡም በጎቻቸውን፣ ፍየሎቻቸውንና ከብቶቻቸውን እንዲሁም ያላቸውን ሁሉ ይዘው መጥተዋል።’ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱ እንስሶችን የማርባት ችሎታ ያላቸው ከብት ጠባቂዎች ናቸው፤ በጎቻቸውንና ፍየሎቻቸውን፥ ከብቶቻቸውን ያላቸውን ንብረት ሁሉ ይዘው መጥተዋል’ ብዬ ልንገረው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም ከብት ጠባቂዎች፥ መንጋ አርቢዎች ናቸው፤ በጎቻቸውንና ላሞቻቸውን፥ ያላቸውንም ሁሉ አመጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም በግ የሚጠብቁ ሰዎች ናቸው እነርስሳ ያረቡ ነበርና በጎቻቸውንና ላሞቻቸውን ያላቸውንም ሁሉ አመጡ። |
የያዕቆብ ትውልድ ታሪክ እንደሚከተለው ነው፤ ዮሴፍ የዐሥራ ሰባት ዓመት ወጣት በነበረበት ጊዜ ከአባቱ ሚስቶች ከባላና ከዚልፋ ከተወለዱት ወንድሞቹ ጋር በጎችና ፍየሎች ይጠብቅ ነበር፤ የእነርሱንም ክፋት ነገር ዮሴፍ ወደ አባታቸው አመጣ።
ዮሴፍም ወንድሞቹንና የአባቱን ቤተ ሰዎች እንዲህ አላቸው፦ “እኔ መጥቼ ለፈርዖን፦ ‘እንግዲህ በከነዓን ምድር የነበሩት ወንድሞቼና የአባቴ ቤት ሰዎች ወደ እኔ መጥተዋል፥
በግ ጠባቂ ሁሉ ለግብጽ ሰዎች ርኩስ ነውና፥ በጌሤም እንድትቀመጡ፦ ‘እኛ አገልጋዮችህ ከብላቴናነታችን ጀምረን እስከ አሁን ድረስ፥ እኛም አባቶቻችንም፥ እንስሳ አርቢዎች ነን’ በሉት።”
ፈርዖንም ወንድሞቹን፦ “ሥራችሁ ምንድነው?” አላቸው። እነርሱም ፈርዖንን፦ “እኛ አገልጋዮችህ፥ እኝም አባቶቻችንም፥ በግ አርቢዎች ነን” አሉት።
ሙሴም የምድያን ካህን የሆነውን የአማቹን የይትሮን በጎች ያሰማራ ነበር፤ በጎቹን ከምድረ በዳው ማዶ ነዳቸው፥ ወደ እግዚአብሔርም ተራራ ወደ ኮሬብ መጣ።
ቀጥሎም እሴይን፥ “ልጆችህ እነዚሁ ብቻ ናቸውን?” ሲል ጠየቀው። እሴይም፥ “የሁሉም ታናሽ ገና አልመጣም፤ ነገር ግን በጎች እየጠበቀ ነው” ብሎ መለሰ። ሳሙኤልም እሴይን፥ “በል ልከህ አስመጣው፤ እስኪመጣ ድረስ አንቀመጥም” አለው።