ዘፍጥረት 46:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጌሴም ምድር እንዲቀበለው ያዕቆብ ይሁዳን ወደ ዮሴፍ አስቀድሞ ላከው፤ ወደ ጌሤም ምድርም ደረሱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያዕቆብም ወደ ጌሤም ለመሄድ መመሪያን ይቀበል ዘንድ ይሁዳን አስቀድሞ ወደ ዮሴፍ ላከው። እነርሱም ጌሤም ሲደርሱ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጌሴም ምድር እንዲቀበለው ያዕቆብ ይሁዳን ወደ ዮሴፍ አስቀድሞ ላከው፤ እነርሱ ጌሴም በደረሱ ጊዜ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይሁዳንም ኤሮስ በምትባል በራምሴ ከተማ እንዲቀበለው በፊቱ ወደ ዮሴፍ ላከው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይሁዳንም በጌሤም እንዲቀበለው በፊቱ ወደ ዮሴፍም ላከ ወደ ጌሤም ምድርም ደረሱ። |
ይሁዳም አባቱን እስራኤልን እንዲህ አለው “ልጁን ከእኔ ጋር ስደደው፤ እኛም በቶሎ እንሂድ፤ ይህ ከሆነ፥ አንተም፥ እኛም፥ ልጆቻችንም አንሞትም፤ እንተርፋለን።
በግ ጠባቂ ሁሉ ለግብጽ ሰዎች ርኩስ ነውና፥ በጌሤም እንድትቀመጡ፦ ‘እኛ አገልጋዮችህ ከብላቴናነታችን ጀምረን እስከ አሁን ድረስ፥ እኛም አባቶቻችንም፥ እንስሳ አርቢዎች ነን’ በሉት።”
ዮሴፍም ወደ ፈርዖን ሄዶ “አባቴና ወንድሞቼ በጎቻቸውንና ፍየሎቻቸውን ከብቶቻቸውንና ሌላም ያላቸውን ነገር ሁሉ ይዘው ከከነዓን ወደዚህ መጥተዋል፤ አሁንም በጌሴም ምድር ይገኛሉ” አለው።