La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 44:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ይህ ጌታዬ የሚጠጣበት፥ የተሰወረ ነገርም የሚያውቅበት ጽዋ አይደለምን? የፈጸማችሁት ድርጊት ክፉ ነው’” በላቸው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ይህ ጌታዬ የሚጠጣበት፣ የተሰወረ ነገርም የሚያውቅበት ጽዋ አይደለምን? የፈጸማችሁት ድርጊት ክፉ ነው’ ” በላቸው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የጌታዬን የብር ዋንጫ የሰረቃችሁት ለምንድን ነው? ዋንጫው ጌታዬ የሚጠጣበትና ሁሉን ነገር መርምሮ የሚያውቅበት እንደ ሆነ አታውቁምን? ይህ ያደረሳችሁት በደል እጅግ ከባድ ነው’ ብለህ ንገራቸው።”

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ጌታዬ የሚ​ጠ​ጣ​በ​ትን፥ ምስ​ጢ​ር​ንም የሚ​ያ​ው​ቅ​በ​ትን የብር ጽዋ ለምን ሰረ​ቃ​ችሁ? ባደ​ረ​ጋ​ች​ሁት ነገር በደ​ላ​ችሁ።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ስለ ምን ክፋን መለሳችህ? ጌታዬ የሚጠጣበት ምሥጢርንም የሚያውቅበት ጽዋ አይደለምን? ባደረጋችሁች ነገር በደላችሁ።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 44:5
7 Referencias Cruzadas  

ላባም፦ “በዓይንህ ፊት ሞገስን የማገኝ ብሆንስ ከዚህ ተቀመጥ፥ እግዚአብሔር በአንተ ምክንያት እንደ ባረከኝ ተመልክቼአለሁና” አለው።


ዮሴፍም፥ “ለምን እንዲህ ያለ ነገር አደረጋችሁ? እንደ እኔ ያለ ሰው ስውር ነገርን የሚያውቅበት ልዩ ጥበብ እንዳለው አታውቁምን?” ሲል ጠየቃቸው።


የቤቱ አዛዥም እንደ ደረሰባቸው፥ ልክ እንደተባለው ተናገራቸው።


የንጉሥ ቤንሀዳድ ባለሟሎች የምሕረት መልእክት ይጠባበቁ ስለ ነበር፥ አክዓብ “ወንድሜ” ሲል በሰሙ ጊዜ ወዲያውኑ ቀበል አድርገው “አንተ እንዳልከው ቤንሀዳድ በእርግጥ ወንድምህ ነው!” አሉት። አክዓብም “ወደ እኔ አምጡት!” አላቸው። ቤንሀዳድም በመጣ ጊዜ፥ አክዓብ ወደ ሠረገላው ገብቶ እንዲቀመጥ ቤንሀዳድን ጋበዘው።


የገዛ ልጁንም መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ፤ እርሱም ራሱ ሟርተኛና አስማተኛ ሆኖ ከጠንቋዮችና ከሙታን ጠሪዎች ምክርን ይጠይቅ ነበር፤ በዚህም ሁሉ አድራጎቱ ታላቅ ኃጢአት በመሥራቱ የእግዚአብሔርን ቁጣ አነሣሣ።


“ከደሙ ጋር ምንም ዓይነት ነገር አትብሉ፤ ሞራ ገላጭም አትሁኑ፥ አስማትም አታድርጉ።