Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፍጥረት 44:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ከከተማው ምንም ያህል ርቀው ሳይሄዱ፥ ዮሴፍ የቤቱን አዛዥ እንዲህ አለው፦ “እነዚያን ሰዎች ቶሎ ድረስባቸውና፥ ‘ለበጎ ነገር ስለምን ክፉ መለሳችሁ?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ከከተማው ምንም ያህል ርቀው ሳይሄዱ፣ ዮሴፍ የቤቱን አዛዥ እንዲህ አለው፤ “እነዚያን ሰዎች ቶሎ ድረስባቸውና፣ ‘ለበጎ ነገር ስለ ምን ክፉ መለሳችሁ?

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ከከተማው ወጥተው ገና ጥቂት መንገድ ርቀው እንደ ሄዱ፥ ዮሴፍ የቤቱን አዛዥ እንዲህ አለው፤ “እነዚያን ሰዎች ተከታትለህ ያዛቸው፤ ወደ እነርሱም ስትደርስ ‘በመልካም ፈንታ ክፉ የመለሳችሁት ስለምንድን ነው?

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ከከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ወጥ​ተው ገና ሳይ​ርቁ ዮሴፍ ለቤቱ አዛዥ እን​ዲህ አለ፥ “ተነ​ሥ​ተህ ሰዎ​ቹን ተከ​ት​ለህ ያዛ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ በመ​ል​ካሙ ፈንታ ስለ​ምን ክፉን መለ​ሳ​ችሁ?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ከከተማይቱም ወጥተው ገና ሳይርቁ ዮሴፍ ለቤቱ አዛዥ እንዲህ አለ፦ ተነሥተህ ሰዎቹና ተከተላቸው በደረስህባቸውም ጊዜ እንዲህ በላቸው፦ በመልካሙ ፋንታ፥

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 44:4
9 Referencias Cruzadas  

ኢየሱስ “ከአባቴ ብዙ መልካም ሥራ አሳየኋችሁ፤ ከእነርሱ ስለ የትኛው ሥራ ትወግሩኛላችሁ?” ብሎ መለሰላቸው።


በበጎ ፈንታ ክፋትን መለሱልኝ፥ ለብቻዬም ቀረሁ።


በመልካም ፋንታ ክፉን የሚመልስ፥ ክፉ ነገር ከቤቱ አትርቅም።


በመልካም ፋንታ ክፉን፥ በፍቅር ፋንታ ጠላትነትን መለሱልኝ።


እነሆ፥ ለበጎነታችን ክፋት ይመልሱልናል፤ ከሰጠኸንም ርስት ሊያወጡን መጥተዋል።


ዳዊት ይህን ተናግሮ ሲያበቃ ሳኦል፥ “ልጄ ዳዊት ሆይ፤ ይህ የአንተ ድምፅ ነውን?” ሲል ጠየቀው፤ ሳኦል ጮኾም አለቀሰ።


“እንዲህም ሆነ፥ ጦረኞቹ ከጠፉ ከሕዝቡም መካከል ከሞቱ በኋላ፥


ጎሕ ሲቀድ ሰዎቹ ከነአህዮቻቸው ተሸኙ።


በዚህ ጊዜ ልብሳቸውን በኀዘን ቀደዱ፤ ሁሉም ስልቾቻቸውን በየአህዮቻቸው ጭነው ወደ ከተማዪቱ ተመለሱ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios