እነሆ እኛ በእርሻ መካከል ነዶ ስናስር ነበር፥ እነሆም፥ የእኔ ነዶ ቀጥ ብላ ቆመች፥ የእናንተም ነዶች በዙሪያ ከብበው እነሆ ለእኔ ነዶ ሰገዱ።”
ዘፍጥረት 43:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም መልሰው፥ “አገልጋይህ አባታችን አሁንም በሕይወት አለ፤ ደኅና ነው” በማለት ወደ መሬት ዝቅ ብለው በአክብሮት እጅ ነሡት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም መልሰው፣ “አገልጋይህ አባታችን አሁንም በሕይወት አለ፤ ደኅና ነው” በማለት ወደ መሬት ዝቅ ብለው በአክብሮት እጅ ነሡት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም “አገልጋይህ አባታችን በሕይወት አለ፤ ጤንነቱም የተሟላ ነው” አሉት። ወደ መሬት ዝቅ ብለውም እጅ ነሡት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም አሉት፥ “ባሪያህ ሽማግሌው አባታችን ደኅና ነው፤ ገና በሕይወት አለ።” ዮሴፍም አለ፥ “ሰውየው እግዚአብሔር የባረከው ነው።” ራሳቸውንም ዝቅ አድርገው ሰገዱለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱ አሉት፦ ባሪያህ አባታችን ደኅና ነው ገና በሕወይት አለ፤ አጎንብሰውም ሰገዱለት። |
እነሆ እኛ በእርሻ መካከል ነዶ ስናስር ነበር፥ እነሆም፥ የእኔ ነዶ ቀጥ ብላ ቆመች፥ የእናንተም ነዶች በዙሪያ ከብበው እነሆ ለእኔ ነዶ ሰገዱ።”
በሦስተኛውም ቀን፥ እነሆ፥ የተቀደደ ልብስ የለበሰ፥ በራሱም ላይ ትቢያ የነሰነሰ አንድ ሰው ከሳኦል ሰፈር መጣ። ወደ ዳዊት መጥቶም በግምባሩ በመደፋት እጅ ነሣ።