ዘፍጥረት 42:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እህላቸውን በአህዮቻቸው ጭነው ጉዞአቸውን ቀጠሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እህላቸውን በአህዮቻቸው ጭነው ጕዟቸውን ቀጠሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዮሴፍ ወንድሞች የገዙትን እህል በአህዮቻቸው ጭነው ጒዞ ጀመሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም እህሉን በአህዮቻቸው ላይ ጫኑ፤ ከዚያም ተነሥተው ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም እህሉን በአህዮቻቸው ላይ ጫኑ ከዚያም ተነሥተው ሄዱ። |
ታናሽ ወንድማችሁን ግን ይዛችሁ መምጣት አለባችሁ፤ በዚህም የተናገራችሁት ቃል እውነተኛነት ይረጋገጣል፤ እናንተም ከመሞት ትተርፋላችሁ።” እነርሱም ይህንኑ ለመፈጸም ተስማሙ።
በስልቻዎቻቸው እህል እንዲሞሉላቸው፤ ብሩንም በያንዳንዱ ሰው ስልቻ ውስጥ መልሰው እንዲያስቀምጡና ለጉዞአቸው ስንቅ እንዲያሲዟቸው ዮሴፍ ትእዛዝ ሰጠ። ይህም ከተደረገላቸው በኋላ፥