ዘፍጥረት 41:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህ በኋላ ግን በተከታታይ ሰባት የራብ ዓመታት ይሆናሉ። የራቡ ዘመን አገሪቱን እጅግ ስለሚጐዳት፥ በግብጽ የነበረው ያለፈው የጥጋብ ዘመን ሁሉ ጨርሶ አይታወስም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ ግን በተከታታይ ሰባት የራብ ዓመታት ይሆናሉ። የራቡ ዘመን አገሪቱን እጅግ ስለሚጐዳት፣ በግብጽ የነበረው ያለፈው የጥጋብ ዘመን ሁሉ ጨርሶ አይታወስም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያ በኋላ ሰባት የራብ ዓመቶች ይመጣሉ፤ ራብ አገሪቱን በብርቱ ስለሚጐዳት እነዚያ የጥጋብ ዓመቶች ይረሳሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግሞም ከዚህ በኋላ ሰባት የራብ ዓመት ይመጣል፤ በግብፅ ሀገር ሁሉ የነበረውንም ጥጋብ ሁሉ ይረሱታል፤ ራብም ምድርን ሁሉ ያጠፋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞ ከዚህ በኍላ የሰባት ዓመት ራብ ይመጣል በግብፅ አገር የነበረውም ጥጋብ ሁሉ ይረሳል ራብም ምድርን በጣም ያጠፋል |
ከእነርሱም በኋላ ዐጥንታቸው የወጣ አስከፊ መልክ ያላቸው ሰባት ላሞች፥ ሰባት ዓመታት ናቸው፤ እንደዚሁም ፍሬ አልባ የሆኑትና በምሥራቅ ነፋስ ተመትተው የደረቁት ሰባት የእሸት ዛላዎች ሰባት የራብ ዓመታት ናቸው።
ራቡ በአገሩ ላይ እየተስፋፋ ስለ ሄደ፥ ዮሴፍ ጐተራዎቹን ከፍቶ እህሉ ለግብፃውያን እንዲሸጥ አደረገ፤ ምክንያቱም ራቡ በመላዪቱ ግብጽ ጸንቶ ነበር።
ስለዚህም ጋድ ወደ ዳዊት ሄዶ፥ “በምድርህ ሦስት ዓመት ራብ ከሚሆን፥ ለሦስት ወር ጠላቶችህ ከሚያሳድዱህና በምድርህ ላይ ለሦስት ቀን የቸነፈር መቅሠፍት ከሚሆን የትኛውን ትመርጣለህ? እንግዲህ አሁን ለላከኝ ምን መልስ እንደምሰጥ አስበህበት ወስን” አለው።
በገለዓድ የምትገኘው የቱቢ ተወላጅ የሆነውና ኤልያስ ተብሎ የሚጠራው ነቢይ፤ ንጉሥ አክዓብን “በእኔ ቃል ካልሆነ በቀር በሚቀጥሉት ዓመቶች በምድር ላይ ጠል ወይም ዝናብ እንደማይኖር እኔ በማገለግለው በእስራኤል አምላክ፥ በሕያው ጌታ ስም እነግርሃለሁ” አለው።
ልጇን ከሞት ያስነሣላትን፥ በሱነም ትኖር የነበረችውን ሴት እነሆ፥ ኤልሳዕ አስቀድሞ እንዲህ ሲል ነግሮአት ነበር፥ “እግዚአብሔር እስከ ሰባት ዓመት የሚቆይ ራብ በዚህች ምድር ላይ ልኮአል፤ ከቤተሰብሽ ጋር በሕይወት ለመትረፍ ከዚህ ተነሥተሽ ወደ ሌላ ስፍራ ሂጂ።”
እንዲሁም በምድር ላይ የተባረከ በእውነት አምላክ ይባረካል፥ በምድርም ላይ የማለ በእውነት አምላክ ይምላል፤ ምክንያቱም የቀድሞው ጭንቀት ተረስቶአል፥ ከዓይኔም ተሰውሮአል።
ነገር ግን በእውነት እላችኋለሁ፤ በኤልያስ ዘመን ሦስት ዓመት ከስድስት ወር ሰማይ ተዘግቶ ሳለ፥ በምድር ሁሉ ላይ ብርቱ ራብ በነበረ ጊዜ፥ በእስራኤል ብዙ መበለቶች ነበሩ፤