Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 65:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 እንዲሁም በምድር ላይ የተባረከ በእውነት አምላክ ይባረካል፥ በምድርም ላይ የማለ በእውነት አምላክ ይምላል፤ ምክንያቱም የቀድሞው ጭንቀት ተረስቶአል፥ ከዓይኔም ተሰውሮአል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ስለዚህ በምድሪቱ ላይ በረከትን የሚጠራ፣ በእውነት አምላክ ስም ይባረካል፤ በምድሪቱ መሐላን የሚምል፣ በእውነት አምላክ ስም ይምላል፤ ያለፉት ችግሮች ተረስተዋል፤ ከዐይኖቼም ተሰውረዋል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 የቀድሞው ችግር ስለ ተረሳና ከዐይኔ ስለ ተሰወረ በሀገሪቱ በረከትን የሚለምን በእኔ በታማኙ እግዚአብሔር ስም ይለምናል፤ በሀገሪቱም የሚምሉ በእኔ በታማኙ እግዚአብሔር ስም ይምላሉ።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 እን​ዲ​ሁም በም​ድር ላይ የተ​ባ​ረኩ ይሆ​ናሉ፤ እው​ነ​ተ​ኛ​ውን አም​ላክ ያመ​ሰ​ግ​ና​ሉና፥ በም​ድ​ርም ላይ በእ​ው​ነ​ተ​ኛው አም​ላክ ይም​ላ​ሉና፤ የቀ​ድ​ሞ​ው​ንም ጭን​ቀት ረስ​ተ​ዋ​ልና፤ በል​ቡ​ና​ቸ​ውም አያ​ስ​ቡ​ት​ምና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 እንዲሁም በምድር ላይ የተባረከ በእውነት አምላክ ይባረካል፥ በምድርም ላይ የማለ በእውነት አምላክ ይምላል፥ የቀድሞው ጭንቀት ተረስቶአልና፥ ከዓይኔም ተሰውሮአልና።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 65:16
34 Referencias Cruzadas  

‘በሕያው ጌታ እምላለሁ!’ ብለህም በእውነትና በቅንነት በጽድቅም ብትምል፥ አሕዛብ እራሳቸውን በእርሱ ይባርካሉ በእርሱም ይመካሉ።”


በዚያ ቀን በግብጽ ምድር በከንዓን ቋንቋ የሚናገሩ፥ በሠራዊት ጌታም የሚምሉ አምስት ከተሞች ይሆናሉ፤ ከነዚህም አንዷ የጥፋት ከተማ ተብላ ትጠራለች።


አንተ መታመኛዬ ነህና ከደበቁብኝ ወጥመድ አውጣኝ።


ዙፋኖችንም አየሁ፤ በእነርሱም ላይ ለተቀመጡት የመፍረድ ሥልጣን ተሰጣቸው፤ ስለ ኢየሱስም ምስክርነትና ስለ እግዚአብሔር ቃል ራሶቻቸው የተቈረጡባቸውን ሰዎች ነፍሳት፥ እንዲሁም ለአውሬውና ለምስሉም ያልሰገዱትን ምልክቱንም በግምባራቸው በእጆቻቸውም ላይ ያልተቀበሉትን አየሁ፤ እንደገና ሕያው ሆነው ከክርስቶስም ጋር ለሺህ ዓመት ነገሡ።


መላስ ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር እንዲሆን ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደሆነ እንዲመሰክሩ ነው።


“እኔ ሕያው ነኝ፤” ይላል ጌታ፤ “ጉልበት ሁሉ ለእኔ ይንበረከካል፤ ልሳንም ሁሉ እግዚአብሔርን ያመሰግናል፤” ተብሎ ተጽፎአልና።


ኢየሱስም “እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በኩል ካልሆነ ማንም ወደ አብ የሚመጣ የለም።


ሕግ በሙሴ ተሰጥቶ ነበርና፤ ጸጋና እውነት ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ሆነ።


እኔም በኢየሩሳሌም ሐሤት አደርጋለሁ በሕዝቤም ደስ ይለኛል፤ ከዚያም ወዲያ የልቅሶ ድምፅና የዋይታ ድምፅ አይሰማባትም።


“እርሱ ዐለት፥ ሥራውም ፍጹም ነው፤ መንገዱም ሁሉ የቀና ነው፥ የታመነ አምላክ፥ ተንኮል የሌለበት፥ እርሱ ቀጥተኛና ጻድቅ ነው።


ቃልም ሥጋ ሆነ፤ በእኛም ዘንድ አደረ፤ ጸጋንና እውነትን የተመላውን፥ የአባቱ አንድያ ልጅ በአባቱ ዘንድ ያለውን ክብሩንም አየን።


በሰገነትም ላይ ለሰማያት ሠራዊት የሚሰግዱትን፥ ለጌታ የሚሰግዱትንና በእርሱም የሚምሉትን፥ በንጉሣቸውም ደግሞ የሚምሉትን፥


ይመጣሉ በጽዮንም ተራራ ላይ ሆነው እልል ይላሉ፤ ስለ ጌታም በጎነቱ፥ ስለ እህሉና ስለ ወይን ጠጁ፥ ስለ ዘይቱም፥ ስለ በጎቹና ስለ ከብቶቹ በሐሤት ይሞላሉ፤ ነፍሳቸውም ውኃ ጠጥታ እንደ ረካች ገነት ትሆናለች፥ ከእንግዲህም ወዲህ አያዝኑም።


በበዓል እንዲምል ሕዝቤን እንዳስተማሩ በስሜ፦ ‘በሕያው ጌታ እምላለሁ!’ ብለው እንዲምሉ የሕዝቤን መንገድ በትጋት ቢማሩ፥ በዚያን ጊዜ በሕዝቤ መካከል ይመሠረታሉ።


ጌታ ግን እውነተኛ አምላክ ነው፤ እርሱም ሕያው አምላክና የዘለዓለም ንጉሥ ነው፤ ከቁጣው የተነሣ ምድር ትንቀጠቀጣለች፤ አሕዛብም መዓቱን መቋቋም አይችሉም።


አታፍሪምና አትፍሪ፤ አትዋረጂምና አትደንግጪ፤ የሕፃንነትሽንም እፍረት ትረሺዋለሽ፥ የመበለትነትሽንም ስድብ ከእንግዲህ ወዲህ አታስቢም።


እናንተ በእስራኤል ስም የተጠራችሁ ከይሁዳም ውኆች የወጣችሁ፥ በጌታ ስም የምትምሉ፥ በእውነት ሳይሆን በጽድቅም ሳይሆን የእስራኤልን አምላክ የምትጠሩ፥


ጌታም የተቤዣቸው ይመለሳሉ፥ እየዘመሩም ወደ ጽዮን ይመጣሉ፤ የዘላላም ደስታ በራሳቸው ላይ ይሆናል፤ ሐሤትንና ደስታን ያገኛሉ፥ ኀዘንና ትካዜም ይሸሻሉ።


እስራኤል ከግብጽ በወጣ ጊዜ እንደ ሆነው ሁሉ፤ ከአሦር ለተረፈው ቅሬታ ሕዝብ፤ እንዲሁ ጐዳና ይዘጋጅለታል።


አቤቱ፥ አንተ ግን መሓሪና ርኅሩኅ አምላክ ነህ፥ ለቁጣ የዘገየህ፥ ጽኑ ፍቅርህና እውነትህ የበዛ፥


ስሙ ለዘለዓለም ይታወስ፥ እንደ ፀሐይ ዕድሜ ስሙ ጸንቶ ይኑር፥ የምድር አሕዛብ ሁሉ በርሱ ይባረኩ፥ አሕዛብ ሁሉ ያመሰግኑት፥


ለሰይፍ እጅ አልፈው ይሰጣሉ፥ የቀበሮም እድል ፈንታ ይሆናሉ።


ጌታ እግዚአብሔርን ፍራ፥ እርሱንም አምልክ፥ ከእርሱም አትነጠል፥ በስሙም ማል።


ጌታ እግዚአብሔርን ፍራ፤ እርሱንም አምልክ፥ በስሙም ማል።


ጌታም በፊቱ አልፎ እንዲህ ብሎ አወጀ፦ “ጌታ፥ ጌታ፥ መሓሪ አምላክ፥ ሞገስ ያለው፥ ታጋሽ፥ ፅኑ ፍቅሩና እውነቱ የበዛ፥


መከራህንም ትረሳለህ፥ እንዳለፈ ውኃ ታስበዋለህ።


ፈጣሪሽ ባልሽ ነው፥ ስሙም የሠራዊት ጌታ ነው፤ የእስራኤልም ቅዱስ ታዳጊሽ ነው፥ እርሱም የምድር ሁሉ አምላክ ይባላል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios