ዘፍጥረት 39:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እያደርም የጌታው ሚስት ዐይኗን ጣለችበት፤ አፍ አውጥታም፥ “አብረኸኝ ተኛ” አለችው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እያደርም የጌታው ሚስት በዮሴፍ ላይ ዐይኗን ጣለች፤ አፍ አውጥታም፣ “ዐብረኸኝ ተኛ” አለችው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከጊዜ በኋላ የጌታው ሚስት ዮሴፍን ተመልክታ ስለ አፈቀረችው፥ “ና ከእኔ ጋር አብረን እንተኛ” አለችው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚህም በኋላ እንዲህ ሆነ፤ የጌታው ሚስት በዮሴፍ ላይ ዐይንዋን ጣለችበት፤ “ከእኔም ጋር ተኛ” አለችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚህም በኍላ እንዲህ ሆነ የጌታው ሚስት በዮሴፍ ላይ ዓይንዋን ጣለች፦ ከእኔም ጋር ተኛ አለችው። |
በየመንገዱ ራስ ሁሉ ላይ ከፍ ያለውን ቦታሽን ሠራሽ፥ ውበትሽንም አረከስሽ፥ ለአላፊ አግዳሚው ሁሉ እግርሽን ከፈትሽ፥ አመንዝራነትሽንም አበዛሽ።