Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሕዝቅኤል 16:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 በባሏ ፋንታ ሌሎችን የምታስተናግድ አመንዝራ ሴት ሆነሻል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 “ ‘አንቺ ከገዛ ባሏ ይልቅ ሌሎችን የምታስተናግድ አመንዝራ ነሽ!

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 አንቺ፥ ዘማዊት ሚስት! ባልዋን ማፍቀር ትታ ከባዕዳን ጋር እንደምታመነዝር ሴት ሆንሽ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 ከባ​ልዋ ገን​ዘብ ተቀ​ብላ የም​ታ​መ​ነ​ዝር ሴትን ትመ​ስ​ያ​ለሽ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 በባልዋ ፋንታ ሌሎችን ተቀብላ የምታመነዝር ሴትን ትመስያለሽ።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 16:32
15 Referencias Cruzadas  

ለራስህ የሠራሃቸው አማልክትህ ወዴት ናቸው? ይሁዳ ሆይ! አማልክትህ እንደ ከተሞችህ ቍጥር ብዛት እንዲሁ ናቸውና እስቲ ይነሡ በመከራህም ጊዜ ያድኑህ።


ጌታም እንዲህ አለኝ፦ “የእስራኤል ልጆች ወደ ሌሎች አማልክት ቢመለሱና የዘቢብ ጥፍጥፍን ቢወድዱ እንኳ ጌታ እንደሚወድዳቸው እንዲሁ አንተም ዳግመኛ ሂድ፥ በውሽማዋ የምትወደደውን አመንዝራይትን ሴት ውደድ።”


የይሁዳ ልጆችና የእስራኤል ልጆች በአንድነት ይሰበሰባሉ፥ እነርሱም አንድ አለቃ በራሳቸው ላይ ይሾማሉ፤ የኢይዝራኤልም ቀን ታላቅ ይሆናልና ከምድሪቱ ይወጣሉ።


ጻጽቃን ሰዎች በአመንዝሮቹና በደም አፍሳሾቹ ሴቶች ላይ በሚፈረደው ፍርድ ይፈርዱባቸዋል፤ ምክንያቱም አመንዝሮች ናቸውና፥ ደምም በእጃቸው አለና።


አመንዝረዋልና፥ ደምም በእጃቸው አለና፤ ከጣዖቶቻቸው ጋር አመንዝረዋል፤ ለእኔ የወለዷቸውን ልጆቻቸውን እንኳ መብል እንዲሆኑ አሳልፈው ሰጥተዋቸዋል።


በአንቺ በኩል አለፍሁ፥ አየሁሽም፥ እነሆ ጊዜሽ የፍቅር ጊዜ ነበር፥ እኔም መጐናጸፊያዬን በላይሽ ላይ ዘረጋሁና ዕርቃንሽን ሸፈንሁ፥ ማልሁልሽም ከአንቺም ጋር ቃል ኪዳን ገባሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ አንቺም የእኔ ሆንሽ።


የእስራኤል ቤት ሆይ! በእውነት ሚስት ባልዋን እንደምታታልል እንዲሁ አታለላችሁኝ ይላል ጌታ።’”


በባዶ እግርሽ ከመሄድ፥ ጉሮሮሽንም ከውኃ ጥም ከልክዪ፤ አንቺ ግን፦ ‘ተስፋ የለኝም፥ አይሆንም! እንግዶችን ወድጄአለሁና፥ እከተላቸዋለሁም’ አልሽ።


እነሆ፦ “ሰው ሚስቱን ቢፈታ፥ ከእርሱም ብትሄድ ሌላም ወንድ ብታገባ፥ በውኑ በድጋሚ ወደ እርሷ ይመለሳልን? ያች ምድር እጅግ የረከሰች አትሆንምን? አንቺ ከብዙ ውሽሞች ጋር አመንዝረሻል፥ ወደ እኔም ትመለሻለሽን? ይላል ጌታ።


አመንዝሮች ሆይ! ከዓለም ጋር ወዳጅ መሆን የእግዚአብሔር ጠላትነት መሆኑን አታውቁምን? ስለዚህ የዓለም ወዳጅ መሆን የሚፈልግ ሁሉ የእግዚአብሔር ጠላት ሆኖአል።


በየመንገዱ ራስ የምንዝርናሽን ስፍራ ሠርተሻል በየአደባባዩም ከፍ ያለውን ቦታሽን አድርገሻል። ዋጋዋን እንደምትንቅ እንደ ጋለሞታ አልሆንሽም።


ለአመንዝራዎች ሁሉ ሥጦታ ይሰጡአቸዋል፥ አንቺ ግን ለወዳጆችሽ ሁሉ ሥጦታሽን ትሰጫለሽ፥ ለአመንዝራነትሽ ከየአቅጣጫው ወደ አንቺ እንዲገቡ ጉቦ ትሰጫቸዋለሽ።


ባለቤቴ በቤቱ የለምና፥ ወደ ሩቅ መንገድ ሄዶአልና፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios