ዘፍጥረት 36:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዓዳ ለዔሳው ኤልፋዝን ወለደች፥ ባሴማትም ራዑኤልን ወለደች፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዓዳ ለዔሳው ኤልፋዝን ወለደችለት፤ ቤሴሞት ደግሞ ራጉኤልን ወለደችለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዓዳ ለዔሳው ኤሊፋዝን ወለደችለት፤ ባሴማትም ረዑኤልን ወለደችለት፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሐዳሶ ለእርሱ ኤልፋዝን ወለደች፤ ቤሴሞትም ራጉኤልን ወለደች፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዓዳ ለዔሳው ኤልፋዝን ወለደች ቤሴሞትም ራጉኤልን ወለደች፤ |
ሦስቱ የኢዮብ ወዳጆች ይህን የደረሰበትን ክፉ ነገር ሁሉ ሰምተው ከየአገራቸው መጡ፥ እነርሱም ቴማናዊው ኤልፋዝ፥ ሹሐዊው ቢልዳድ፥ ነዕማታዊው ሶፋር ነበሩ። እነርሱም ሊያዝኑለትና ሊያጽናኑት በአንድነት ወደ እርሱ ለመምጣት ተስማሙ።
ሙሴም የሚስቱን አባት የምድያማዊውን የራጉኤልን ልጅ ኦባብን እንዲህ አለው፦ “ጌታ፦ ‘ለእናንተ እሰጣችኋለሁ’ ወዳለው ስፍራ እንሄዳለን፤ ጌታ ለእስራኤል መልካምን ነገር ተናግሮአልና አንተ ከእኛ ጋር ና፥ መልካምን እናደርግልሃለን።”