ዘፍጥረት 36:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የፅብዖን ልጆችም፦ አያና ዓና ናቸው። ይህ ዓና የአባቱን የፅብዖንን አህዮች ሲጠብቅ በበረሓ ውስጥ የፍል ውሃ ምንጮችን ያገኘ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የፂብዖን ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው፦ አያ እና ዓና፤ ይህ ዓና የአባቱን የፂብዖንን አህዮች ሲጠብቅ፣ የፍል ውሃ ምንጮችን በምድረ በዳ ያገኘ ሰው ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጺባዖን ልጆችም አያ እና ዐና ናቸው። ይህም ዐና የአባቱን አህዮች ሲጠብቅ በበረሓ ውስጥ የፍል ውሃ ምንጮችን ያገኘ ሰው ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሳባቅ ልጆችም እነዚህ ናቸው፤ ኢኣ፥ ዓናን፤ ይህም ዓናን በምድረ በዳ የአባቱን የሳባቅን አህዮች ሲጠብቅ ፍል ውኃዎችን ያገኘ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አያዓና ይህም ዓና በምድረ በዳ የአባቱን የፅብዖንን አህዮች ሲጠብቅ ፍልውኆችን ያገኘ ነው። |
የአቤሴሎምም አገልጋዮች በአምኖን ላይ አቤሴሎም ያዘዛቸውን ፈጸሙ። ከዚያም የንጉሡ ልጆች በሙሉ ተነሥተው በየበቅሎዎቻቸው ላይ ተቀምጠው ሸሹ።
በዚህ ጊዜ አቤሴሎም ከዳዊት ሰዎች ጋር ድንገት ተገናኘ፤ አቤሴሎም በበቅሎ ተቀምጦ ይሄድ ስለ ነበር፥ በቅሎዋ ጥቅጥቅ ያለ ቅርንጫፍ ባለው ትልቅ ባሉጥ ሥር በምታልፍበት ጊዜ፥ የአቤሴሎም ራስ በባሉጡ ቅርንጫፍ ተያዘ፤ የተቀመጠበትም በቅሎ በሥሩ ስታልፍ፥ እርሱ በሰማይና በምድር መካከል ተንጠልጥሎ ቀረ።
ካህኑም ሳዶቅና ነቢዩ ናታን የዮዳሄም ልጅ በናያስ ከሊታውያንና ፈሊታውያንም ወረዱ፥ ሰሎሞንንም በንጉሡ በዳዊት በቅሎ ላይ አስቀምጠው ወደ ግዮን አመጡት።
ንጉሡም ከእርሱ ጋር ካህኑን ሳዶቅንና ነቢዩን ናታንን የዮዳሄንም ልጅ በናያስን ከሊታውያንንና ፈሊታውያንንም ላከ፥ በንጉሡም በቅሎ ላይ አስቀመጡት።
ከዚህም በቀር እያንዳንዱ ገዢ እንደ አስፈላጊነቱ የሚደርስበትን ሠረገላ ለሚስቡ ፈረሶችና ሌላም አገልግሎት ለሚያበረክቱ የጋማ ከብቶች ገብስና ገፈራ ያቀርብ ነበር።
“ሥርዓቴን ጠብቁ። እንስሳህን ከሌላ ዓይነት ዘር ጋር አታዳቅል፤ በእርሻህም ሁለት ዓይነት ዘር አትዝራ፤ ከሁለት ዓይነት ነገር የተሠራ ልብስ አትልበስ።”
በፈረሶች፥ በበቅሎዎች፥ በግመሎች፥ በአህዮች፥ እንዲሁም በዚያም ሰፈር ባሉ እንስሶች ሁሉ ላይ በሰዎች ላይ እንደ ሆነው ዓይነት ቸነፈር በእነርሱም ላይ ይሆናል።