ዘፍጥረት 35:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የራሔል ልጆች፥ ዮሴፍና ብንያም ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የራሔል ልጆች፦ ዮሴፍ፣ ብንያም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የራሔል ልጆች፥ ዮሴፍና ብንያም ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የራሔል ልጆች፤ ዮሴፍ፥ ብንያም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የራሔል ልጆች ዮሴፍ፥ ብንይም፤ |
ዮሴፍ በዐይኑ ሲቃኝ የእናቱን ልጅ ብንያምን አየና፥ “ያ የነገራችሁኝ ታናሽ ወንድማችሁ ይህ ነው?” ብሎ ጠየቃቸው። ብንያምንም፥ “ልጄ፤ እግዚአብሔር ይባርክህ” አለው።
ከዮሴፍ ገበታ ላይ እየተነሣ ለእያንዳንዳቸው ምግብ ሲቀርብ፥ የብንያም ድርሻ ከሌሎቹ አምስት ዕጥፍ ነበር። እነርሱም እንዲህ ባለ ሁኔታ አብረውት ተደሰቱ፤ እስኪረኩም ጠጡ።
የዮሴፍም ልጆች ዕጣ በኢያሪኮ ወንዝ አጠገብ በምሥራቁ በኩል ካለው ከዮርዳኖስ አንሥቶ በምድረ በዳው አድርጎ ከኢያሪኮ በተራራማው አገር በኩል ወደ ቤቴል ወጣ፤
በአማሌቅ ዘንድ ሥር የነበራቸው እነርሱ ከኤፍሬም፥ ብንያም ሆይ፥ በሕዝብህ መካከል ከአንተ በኋላ ወረዱ፥ አለቆች ከማኪር፥ የንጉሥንም ዘንግ የሚይዙ ከዛብሎን ወረዱ።
በከተማይቱ በር አደባባይም የነበሩ ሽማግሌዎችና ሌሎችም ሰዎች ሁሉ፦ “እኛ ምስክሮች ነን፥ ጌታ ይህችን ወደ ቤትህ የምትገባውን ሴት የእስራኤልን ቤት እንደ ሠሩ እንደ ሁለቱ፥ እንደ ራሔልና እንደ ልያ ያድርጋት፥ አንተም በኤፍራታ ባለ ጠጋ ሁን፥ ስምህም በቤተልሔም ይጠራ።