ዘፍጥረት 35:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስራኤልም በዚያች አገር በተቀመጠ ጊዜ ሮቤል ሄደ የአባቱንም ቁባት ባላን ተገናኛት፥ እስራኤልም ሰማ። የያዕቆብም ልጆች ዐሥራ ሁለት ናቸው፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤልም በዚያ ምድር ሳለ፣ ሮቤል ከአባቱ ቁባት ከባላ ጋራ ተኛ፤ እስራኤልም ድርጊቱን ሰማ። ያዕቆብ ዐሥራ ሁለት ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም፦ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያዕቆብ በዚያ ምድር ሲኖር ሳለ፥ ሮቤል ወደ አባቱ ቁባት ወደ ባላ ገባ። ያዕቆብም ይህን ነገር ሰማ። የያዕቆብ ወንዶች ልጆች ዐሥራ ሁለት ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የያዕቆብም ልጆች ዐሥራ ሁለት ናቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስራኤልም በዚያች አገር በተቀመጠ ጊዜ ሮቤል ሄደ የአባቱንም ቁባት ባላን ተገናኛት እስራኤልም ሰማ። |
ዳዊት ኢየሩሳሌም ወዳለው ቤተ መንግሥቱ በተመለሰ ጊዜ፤ ቤተ መንግሥቱን እንዲጠብቁ ትቶአቸው የሄደውን ዐሥሩን ዕቁባቶቹን ወሰደ፤ በአንድ ቤትም ውስጥ እንዲጠበቁ አደረገ። ቀለብ ሰጣቸው፤ ይሁን እንጂ ወደ እነርሱ አልገባም ነበር፤ እነርሱም እስከሞቱበት ጊዜ ድረስ መበለት ሆነው፥ ለብቻቸው ተገልለው ተቀመጡ።
የእስራኤልም በኩር የሮቤል ልጆች እነዚህ ናቸው። እርሱ የበኩር ልጅ ነበረ፤ ነገር ግን የአባቱን ምንጣፍ ስላረከሰ ብኩርናው ለእስራኤል ልጅ ለዮሴፍ ልጆች ተሰጠ፤ ትውልዱ ግን ከብኩርናው ጋር አልተቈጠረም።
የመገረዝንም ኪዳን ሰጠው፤ እንዲሁም ይስሐቅን ወለደ፤ በስምንተኛውም ቀን ገረዘው፤ ይስሐቅም ያዕቆብን ያዕቆብም ዐሥራ ሁለቱን የአባቶችን አለቆች።
በእርግጥ በእናንተ መካከል ዝሙት እንዳለ ይወራል፤ የዚያም ዓይነት ዝሙት በአሕዛብስ እንኳ የማይደረግ ነው፤ ይኸውም የአባቱን ሚስት ያገባ ሰው አለ።
በአማሌቅ ዘንድ ሥር የነበራቸው እነርሱ ከኤፍሬም፥ ብንያም ሆይ፥ በሕዝብህ መካከል ከአንተ በኋላ ወረዱ፥ አለቆች ከማኪር፥ የንጉሥንም ዘንግ የሚይዙ ከዛብሎን ወረዱ።