ዘፍጥረት 34:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሦስተኛም ቀን በሆነ ጊዜ እጅግ ቆስለው እያሉ፥ የዲና ወንድሞች የያዕቆብ ልጆች ስምዖንና ሌዊ እየራሳቸው ሰይፋቸውን ይዘው ሳይፈሩ ወደ ከተማ ገቡ፥ ወንዱንም ሁሉ ገደሉ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሦስተኛውም ቀን የሁሉም ቍስል ገና ትኵስ ሳለ ከያዕቆብ ልጆች ሁለቱ፣ የዲና ወንድሞች ስምዖንና ሌዊ፣ ሰይፋቸውን መዝዘው በድንገት ወደ ከተማዪቱ ገብተው ወንዶቹን በሙሉ ገደሏቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሦስተኛው ቀን ሰዎቹ ገና ከመገረዝ ቊስል ሳይድኑ ከያዕቆብ ልጆች መካከል ሁለቱ የዲና ወንድሞች ስምዖንና ሌዊ ሰይፍ፥ ሰይፋቸውን ይዘው ማንም ሳያውቅባቸው፥ ወደ ከተማ ገቡና ወንዶቹን ሁሉ ገደሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም ሆነ፤ በሦስተኛው ቀን እጅግ ቈስለው ሳሉ ሁለቱ የያዕቆብ ልጆች የዲና ወንድሞች ስምዖንና ሌዊ እየራሳቸው ሰይፋቸውን ይዘው ተደፋፍረው ወደ ከተማ ገቡ፤ ወንዱንም ሁሉ ገደሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሦስተኛም ቀን በሆነ ጊዜ እጅግ ቆስለው ሳሉ የዲና ወንድሞች የያዕቆብ ልጆች ስምዖንና ሌዊ እየራሳቸው ሰይፋቸውን ይዘው ሳይፈሩ ወደ ከተማ ገቡ |
ጌታም ወተትና ማር የምታፈስሰውን ምድር ለእኛ እንዲሰጠን ለአባቶቻቸው የማለላቸውን ምድር እንዳያሳያቸው የማለላቸው፥ የጌታንም ቃል ያልሰሙ፥ ሕዝብ ሁሉ፥ ከግብጽ የወጡ ተዋጊዎች ሁሉ እስኪጠፉ ድረስ የእስራኤል ልጆች አርባ ዓመት በምድረ በዳ ይሄዱ ነበር።