ዘፍጥረት 33:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያዕቆብም፥ ከፓዳን-ኣሪም በተመለሰ ጊዜ፥ በከነዓን ምድር ወዳለችው፥ ሴኬም ከተማ በሰላም መጣ፥ እናም በከተማይቱ ፊት ለፊት ሰፈረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያዕቆብ ከሰሜን ምዕራብ መስጴጦምያ ከተመለሰ በኋላ፣ በከነዓን ወዳለችው ወደ ሴኬም በደኅና ደረሰ፤ በከተማዪቱም ፊት ለፊት ሰፈረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከመስጴጦምያ በተመለሰ ጊዜ በከነዓን ምድር ወዳለችው ወደ ሴኬም በሰላም ደረሰ፤ እዚያም በከተማይቱ ፊት ለፊት በሚገኘው ሜዳ ላይ ሰፈረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያዕቆብም ከሁለቱ ወንዞች መካከል በተመለሰ ጊዜ በከነዓን ምድር ወዳለችው ወደ ሰቂሞን ከተማ ወደ ሴሎም መጣ፤ በከተማዪቱም ፊት ለፊት ሰፈረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያዕቆብም ከሁለት ወንዞች መካከል በተመለሰ ጊዜ በከንዓን ምድር ወዳለችው ወደ ሴኬም ከተማ በደኅንነት መጣ በከተማይቱም ፊት ሰፈረ። |
ላባም ያዕቆብን ደረሰበት፤ ያዕቆብም ድንኳኑን ኮረብታማው አገር ተክሎ ነበር፥ ላባም ከዘመዶቹ ጋር በገለዓድ ኮረብታማው አገር ድንኳኑን ተከለ።
ልያ በፓዳን-ኣሪም በሶርያ ለያዕቆብ የወለደቻቸው ልጆችና፥ ሴቲቱ ልጇ ዲና እነዚህ ናቸው፥ ወንዶችም ሴቶችም ልጆችዋ ሁሉ ሠላሳ ሦስት ናቸው።
እኔም ፓዳን በመጣሁ ጊዜ፥ ወደ ኤፍራታ ለመግባት ጥቂት መንገድ ቀርቶኝ ሳለሁ፥ ራሔል በከነዓን ምድር ሞተችብኝ፥ በዚያም በኤፍራታ መንገድ ላይ፥ ቀበርኋት፥ እርሷም ቤተልሔም ናት።
ጢማቸውን ላጭተው ልብሳቸውንም ቀድደው ገላቸውንም ተልትለው፥ በጌታ ቤት ለማቅረብ የእህል ቁርባንና ዕጣን በእጃቸው ይዘው፥ ሰማንያ ሰዎች ከሴኬምና ከሴሎ ከሰማርያም መጡ።
ኢያሱም የእስራኤልን ነገድ ሁሉ ወደ ሴኬም ሰበሰበ፥ የእስራኤልንም ሽማግሌዎች አለቆቻቸውንም ፈራጆቻቸውንም ሹማምንቶቻቸውንም ጠራ። እነርሱም በጌታ ፊት ቆሙ።