ዘፍጥረት 31:55 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጠዋት በማለዳ ላባ ተነሥቶ የልጅ ልጆቹን እና ሴቶቹን ልጆቹን ሳመ ባረካቸውም፥ ከዚያም ተነሥቶ ወደ ቤቱ ተመለሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በማግስቱም ማለዳ ላባ የልጅ ልጆቹን እንዲሁም ሴቶች ልጆቹን ስሞ መረቃቸው፤ ከዚያም ወደ አገሩ ተመለሰ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በማግስቱ ላባ ጥዋት በማለዳ ተነሥቶ ልጆቹንና የልጅ ልጆቹን በመሳምና በመመረቅ ተሰናበታቸው፤ ከዚያም ተነሥቶ ወደ ቤቱ ተመለሰ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ላባም ማልዶ ተነሥቶ ወንዶችንና ሴቶችን ልጆቹን ሳመ፤ ባረካቸውም፤ ላባም ተመልሶ ወደ ስፍራው ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ላባም ማልዶ ተነሥቶ ወንዶቹንና ሴቶቹን ልጆቹን ሳመ ባረካቸውም ላባም ተመልሶ ወደ ስፍራው ሄደ። |
ላባም ለያዕቆብ መልሶ እንዲህ አለው፥ “ሴቶቹ ልጆች ልጆቼ ናቸው፥ ሕፃናቱም ሕፃናቴ ናቸው፥ መንጎቹም መንጎቼ ናቸው፥ የምታየውም ሁሉ የእኔ ነው። ነገር ግን ዛሬ በእነዚህ በሴቶች ልጆቼና በወለዱአቸው ልጆቻቸው ላይ ምን ላደርግ እችላለሁ?
ንጉሡም፥ “ኪምሃም ከእኔ ጋር ይሻገራል፤ አንተን ደስ የሚያሰኝህንም ሁሉ አደርግለታለሁ፤ ከእኔ የምትፈልገውን ማናቸውንም ነገር ለአንተም አደርግልሃለሁ” አለው።