ዘፍጥረት 31:48 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ላባም፥ “ይህ ክምር በእኔና በአንተ መካከል ዛሬ ምስክር ነው” አለ። ስለዚህም ገለዓድ ብሎ ሰየማት፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ላባም “ይህ ክምር ድንጋይ በእኔና በአንተ መካከል ዛሬ ምስክር ነው” አለው። ገለዓድ ተብሎ የተጠራውም በዚሁ ምክንያት ነው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ላባም “እነሆ፥ ዛሬ ይህ የድንጋይ ካብ በእኔና በአንተ መካከል ምስክር ነው” አለ። ገለዓድ ተብላ የተጠራችበት ምክንያት ለዚህ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ላባም፥ “ይህች ያቆምኋት የድንጋይ ክምር በእኔና በአንተ መካከል ዛሬ ምስክር ናት” አለ። ስለዚህም ስምዋ ወግረ ስምዕ ተባለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ላባም ይህች ክምር በእኔና በአንተ መካከል ዛሬ ምስክር ናት አለ። ስለዚህም ስምዋ ገለዓድ ተባለ ደግሞም ምድዻ ተባለ፦ |
በአርኖን ሸለቆ አጠገብ ካለችው ከአሮዔር፥ ከሸለቆውም ውስጥ ካለችው ከተማ ጀምረን እስከ ገለዓድ ድረስ፥ የትኛይቱም ከተማ አልተቋቋመችንም፤ ጌታ አምላካችን ሁሉን አሳልፎ ሰጠን።
ለሮቤልና ለጋድም ነገዶች ከገለዓድ ጀምሮ እስከ አርኖን ሸለቆ ድረስ፥ የሸለቆውን አማካይ እንደ ወሰን፥ እስከ አሞን ልጆች ዳርቻ እስከ ያቦቅ ወንዝ ድረስ ሰጠሁ፤
ነገር ግን በእኛና በእናንተ መካከል ከእኛም በኋላ በትውልዳችንና በትውልዳችሁ መካከል በሚቃጠል መሥዋዕትና በቁርባን በአንድነትም መሥዋዕታችን ጌታን እንድናገለግል፥ በሚመጣውም ዘመን ልጆቻችሁ ልጆቻንን፦ “በጌታ ዘንድ ድርሻ የላችሁም” እንዳይሉ ምስክር ይሆናል።’
ስለዚህም እንዲህ አልን፦ በሚመጣው ዘመን ለእኛ ወይም ለትውልዳችን ይህን ሲሉ እኛ እንዲህ እንላለን፦ ‘እነሆ፥ አባቶቻችን የሠሩትን የጌታን መሠዊያ ምሳሌ እዩ፤ በእኛና በእናንተ መካከል ምስክር ነው እንጂ የሚቃጠል መሥዋዕትንና ሌላ መሥዋዕትን ለማቅረብ አይደለም።’
ኢያሱም ለሕዝቡ እንዲህ አላቸው፦ “እነሆ፥ የተናገረንን የጌታን ቃል ሁሉ ሰምቶአልና ይህ ድንጋይ ይመሰክርብናል፤ እንግዲህ አምላካችሁን እንዳትክዱ ይህ ምስክር ይሆንባችኋል።”