La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 31:38 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ለሃያ ዓመታት ከአንተ ጋር ነበርሁ፥ በጎችህና ፍየሎችህ አልጨነገፉም፥ የመንጎችህንም ጠቦቶች አልበላሁም፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ሃያ ዓመት ዐብሬህ ኖሬአለሁ፤ በዚህ ጊዜ ውስጥ ከመንጋህ አንድ ጠቦት እንኳ አልበላሁም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከአንተ ጋር መኖር ከጀመርኩ ኻያ ዓመት ሆነኝ፤ በዚህ ጊዜ ውስጥ በጎችህና ፍየሎችህ የጨነገፉበት ጊዜ የለም፤ ከመንጋህም አንድ ጠቦት እንኳ በልቼ አላውቅም፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሃያ አንድ ዓመት በጎ​ች​ህ​ንና ፍየ​ሎ​ች​ህን ስጠ​ብቅ ኖርሁ፥ ከበ​ጎ​ች​ህም ጠቦ​ቶ​ችን አል​በ​ላ​ሁም፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሀያ ዓመት ሙሉ ከአንተ ጋር ነበርሁ በጎችህና ፍየሎችህ አልጨነገፉም የመንጎችህንም ጠቦቶች አልበላሁም አውሬ የሰበረውን አላመጣሁልህም ነበር፤

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 31:38
9 Referencias Cruzadas  

ላባም፦ “በዓይንህ ፊት ሞገስን የማገኝ ብሆንስ ከዚህ ተቀመጥ፥ እግዚአብሔር በአንተ ምክንያት እንደ ባረከኝ ተመልክቼአለሁና” አለው።


እርሱም አለው፦ “እንዴት እንዳገለገልሁህ፥ ከብትህንም እንዴት እንደ ጠበቅሁልህ አንተ ታውቃለህ።


ከእኔ መምጣት በፊት የነበረህ ጥቂት ነበርና፥ ዛሬም እጅግ በዛ፥ ወደ አንተ በመምጣቴም እግዚአብሔር ባረክህ፥ አሁንም እኔ ደግሞ ለቤቴ የምሠራው መቼ ነው?”


በመንጋዎቹ መራቢያ ወራት ዐይኖቼን አነሳሁ፥ በሕልምም በበጎቹ ላይ የሚንጠላጠሉት አውራ ፍየሎች ሽመልመሌ፥ ዝንጉርጉርና ነቊጣ እንደ ነበሩ አየሁ።


አሁንም ዕቃዬን ሁሉ በረበርህ፥ የቤትህስ ሁሉ የሆነ ዕቃ ምን አገኘህ? እነርሱ በእኛ በሁለታችን መካከል ይፈርዱ ዘንድ በዘመዶቼና በዘመዶችህ ፊት አቅርበው።


አውሬ የሰበረውን አላመጣሁልህም ነበር፥ እኔው ራሴ ስለ እርሱ እከፍልህ ነበርሁ፥ በቀን ሆነ በሌሊት ቢሰረቅ፥ ያን ከእጄ ትፈልግ ነበር።


በምድርህ የምትጨነግፍ ወይም መካን አትኖርም፤ የዘመንህን ቍጥር እሞላለሁ።


“የማሕፀንህ ፍሬ፥ የምድርህ አዝመራ፥ የእንስሳትህ ግልገሎች፥ የከብትህ ጥጃ፥ የበግና የፍየል ግልገሎችህም ይባረካሉ።