ዘፍጥረት 31:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያዕቆብም መለሰ ላባንም እንዲህ አለው፥ “ልጆችህን በጉልበት ከእኔ የምትቀማኝ ስለ መሰለኝና ስለ ፈራሁ ይህን አደረግሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያዕቆብም ለላባ እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “ሴቶች ልጆችህን በኀይል ነጥቀህ ታስቀርብኛለህ ብዬ ስለ ፈራሁ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያዕቆብም “ሴቶች ልጆችህን ነጥቀህ ትወስድብኛለህ ብዬ ስለ ፈራሁ ነው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያዕቆብም መለሰ፤ ላባንም እንዲህ አለው፥ “ልጆችህንና ገንዘቤን ሁሉ ከእኔ የምትቀማኝ ስለመሰለኝና ስለፈራሁ ይህን አደረግሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያዕቆብም መለሰ ላባንም እንዲህ አለው፦ ልጆችህን ከእኔ የምትቀማኝ ሰለመሰለኝና ስለፈራሁ ይህን አደረግሁ። |
አምላኮችህን የምታገኝበት ሰው ግን እርሱ ይሙት፥ የአንተ የሆነውም በእኔ ዘንድ ይገኝ እንደሆነ በዘመዶቻችን ፊት ፈልግ፥ ውሰደውም” አለ። ያዕቆብ ራሔል እንደ ሰረቀቻቸው አያውቅም ነበር።