ዘፍጥረት 31:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለምን በስውር ሸሸህ፥ እኔንም አታለልከኝ፥ በደስታና በዘፈንም በከበሮና በበገና እንድሰድድህ ለምን አልነገርኸኝም? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለመሆኑ ለምን ተደብቀህ ሄድህ? ለምንስ አታለልኸኝ? ብትነግረኝ ኖሮ፣ በደስታና በዘፈን በከበሮና በበገና አልሸኝህም ነበር? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳትነግረኝ ተሰውረህ በመሄድ ለምን አታለልከኝ? ነግረኸኝ ቢሆን ኖሮ በከበሮና በመሰንቆ እየተዘፈነ በደስታ በሸኘሁህ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብትነግረኝ ኑሮ በደስታና በሐሴት፥ በዘፈን፥ በከበሮና በበገና በሸኘሁህ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለምን በስውር ሸሸህ? ከእኔም ከድተህ ስለምን ኮበለልህ? በደስታና በዘፈም በከበሮና በበገና እንድሰድድህ ለምን አልነገርኸኝም? |
በግብዣቸው ላይ በገናና መሰንቆ፤ ከበሮና ዋሽንት እንዲሁም የወይን ጠጅ አለ፤ ነገር ግን ለጌታ ሥራ ቦታ አልሰጡም፤ ለእጆቹም ሥራ ክብር አላሳዩም።
ጌዴዎን ከአገልጋዮቹ ዐሥር ሰዎች ወስዶ ጌታ እንዳዘዘው አደረገ፤ ቤተሰቡንና የከተማውን ሰው ስለ ፈራ ይህን ያደረገው ቀን ሳይሆን ሌሊት ነበር።