ዘፍጥረት 30:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልያም፦ ጉድ አለች፥ ስሙንም ጋድ ብላ ጠራችው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልያም፣ “ምን ዐይነት መታደል ነው” አለች፤ ስሙንም ጋድ ብላ አወጣችለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልያም “እንዴት የታደልኩ ነኝ!” ስትል ስሙን ጋድ ብላ ጠራችው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልያም፥ “እኔም ራሴን ብፅዕት አሰኘሁ” ስትል ስሙን ጋድ ብላ ጠራችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልያም፦ ጉድ አለች ስሙንም ጋድ ብላ ጠራችው። |
እናንተን ጌታን የተዋችሁትን ግን፥ ቅዱሱንም ተራራዬን የረሳችሁትን፥ ዕጣ ፋንታ ለተባለ ጣዖትም ማዕድ ያዘጋጃችሁትን፥ ዕድል ለተባለ ጣዖትም የወይን ጠጅ ለመጠጥ ቁርባን የቀዳችሁትን፥
“የጋድ ልጆች በየትውልዳቸው፥ በየወገኖቻቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች፥ እንደየስማቸው ቍጥር፥ ዕድሜው ሀያ ዓመት የሆነውንና ከዚያም በላይ ያለው፥ ወደ ጦርነት የሚወጣው ሁሉ፥