ዘፍጥረት 28:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈራ፥ እንዲህም አለ፦ “ይህ ስፍራ እንዴት ያስፈራ፥ ይህ ስፍራ የእግዚአብሔር ቤት ነው እንጂ ሌላ አይደለም፥ ይህም የሰማይ ደጅ ነው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም በፍርሀት፣ “ይህ ስፍራ እንዴት የሚያስፈራ ነው! ይህስ ሌላ ሳይሆን የእግዚአብሔር ቤት መሆን አለበት፤ የሰማይ ደጅ ነው” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጣም ፈርቶም ስለ ነበር “ይህ እንዴት የሚያስፈራ ቦታ ነው! ይህ የእግዚአብሔር ቤት መሆን አለበት፤ ወደ ሰማይ የሚያስገባው በር ይህ ነው” አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈራ፤ እንዲህም አለ፥ “ይህ ስፍራ እንዴት ያስፈራ፤ ይህ ስፍራ የእግዚአብሔር ቤት ነው እንጂ ሌላ አይደለም፤ ይህችም የሰማይ ደጅ ናት።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈራ፥ እንዲህም አለ፦ ይህ ስፍራ እንዴት ያስፈራ ይህ ስፍራ የእግዚአብሔር ቤት ነው እንጂ ሌላ አይደለም ይህም የሰማይ ደጅ ነው። |
እርሱም፦ “እኔ የአባትህ አምላክ፥ የአብርሃም አምላክ፥ የይስሐቅ አምላክ፥ የያዕቆብም አምላክ ነኝ” አለው። ሙሴም ወደ እግዚአብሔር ማየት ፈርቶ ፊቱን ሸፈነ።
እግዚአብሔር በሰማይ፥ አንተም በምድር ነህና በአፍህ አትቸኩል፥ ልብህም በእግዚአብሔር ፊት ቃልን ለመናገር አይቸኩል፥ ስለዚህም ቃልህ ጥቂት ትሁን።
ሰዎቹም የሆነውን ነገር ለማየት ወጥተው ወደ ኢየሱስ መጡ፤ አጋንንትም የወጡለትን ሰው ለብሶ፥ ልቡም ተመልሶ፥ በኢየሱስ እግር አጠገብ ተቀምጦ አገኙትና ፈሩ።
ይህ ሳይሆን ቀርቶ ብዘገይ ግን፥ በዚህ በጻፍሁልህ ትእዛዝ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን፥ የእውነት ዓምድና መሠረት በሆነችው በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ እንድታውቅ ነው።
ፍርድ ከእግዚአብሔር ቤት ተነሥቶ የሚጀመርበት ጊዜ ደርሶአል፤ በቅድሚያም በእኛ የሚጀመር ከሆነ፥ ለእግዚአብሔር ወንጌል የማይታዘዙ መጨረሻቸው ምን ይሆን?