ታራም ልጁን አብራምን፥ የልጅ ልጁን የሐራንን ልጅ ሎጥንና የልጁንም የአብራምን ሚስት ምራቱን ሣራን ወሰደ፥ ከእርሱም ጋር ወደ ከነዓን ምድር ይሄዱ ዘንድ ከከለዳውያን ዑር ወጡ፥ ወደ ካራንም መጡ፥ ከዚያም ተቀመጡ።
ዘፍጥረት 28:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያዕቆብም ከቤርሳቤህ ወጥቶ ወደ ካራን ሄደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያዕቆብ ከቤርሳቤህ ተነሥቶ ወደ ካራን ሄደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያዕቆብ ቤርሳቤህን ትቶ ወደ ካራን ለመሄድ ተነሣ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያዕቆብም ከአዘቅተ መሐላ ወጥቶ ወደ ካራን ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያዕቆብም ከቤርሳቤህ ወጥቶ ወደ ካራን ሄደ። |
ታራም ልጁን አብራምን፥ የልጅ ልጁን የሐራንን ልጅ ሎጥንና የልጁንም የአብራምን ሚስት ምራቱን ሣራን ወሰደ፥ ከእርሱም ጋር ወደ ከነዓን ምድር ይሄዱ ዘንድ ከከለዳውያን ዑር ወጡ፥ ወደ ካራንም መጡ፥ ከዚያም ተቀመጡ።
አብራምም ሚስቱን ሦራንና የወንድሙን ልጅ ሎጥን፥ ያገኙትን ከብት ሁሉና በካራን ያገኙአቸውን ሰዎች ይዞ ወደ ከነዓን ምድር ለመሄድ ወጣ፥ ወደ ከነዓንም ምድር ገቡ።
ለባርያህ ካሳየኸው ከጽኑ ፍቅርና ከታማኝነትህ ሁሉ ትንሽ ስንኳ የማይገባኝ ነኝ፥ በትሬን ብቻ ይዤ ይህን ዮርዳኖስን ተሻግሬ ነበር፥ አሁን ግን ለሁለት ወገን የተከፈልኩ ሆንሁ።
እግዚአብሔርም ያዕቆብን አለው፦ “ተነሥተህ ወደ ቤቴል ውጣ፥ በዚያም ኑር፥ ከወንድምህ ከዔሳው ፊት በሸሸህ ጊዜ ለተገለጠልህ ለእግዚአብሔርም መሠውያውን ሥራ።”
በዚያም መሠዊያውን ሠራ፥ የዚያንም ቦታ ስም “ኤልቤቴል” ብሎ ጠራው፥ እርሱ ከወንድሙ ፊት በሸሸበት ጊዜ እግዚአብሔር በዚያ ተገልጦለት ነበርና።
ጌታም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ “ሂድ፥ አንተ ከግብጽ ምድር ካወጣኸው ሕዝብ ጋር ከዚህ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ‘ለዘርህ እሰጣታለሁ’ ብዬ ወደ ማልሁባት ምድር ውጣ፤