ዘፍጥረት 27:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያዕቆብም ወደ አባቱ ወደ ይስሕቅ ቀረበ፥ ዳሰሰውም፥ እንዲህም፦ “ይህ ድምፅ የያዕቆብ ድምፅ ነው፥ እጆቹ ግን የዔሳው እጆች ናቸው” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያዕቆብም ወደ አባቱ ወደ ይሥሐቅ ተጠጋ፤ አባቱም በእጁ እየዳሰሰው፣ “ይህ ድምፅ የያዕቆብ ድምፅ ነው፤ እጆቹ ግን የዔሳው እጆች ናቸው” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያዕቆብም ወደ አባቱ ተጠጋ፤ አባቱም ዳሰሰውና “ድምፅህ የያዕቆብን ድምፅ ይመስላል፤ ክንድህ ግን የዔሳውን ክንድ ይመስላል” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያዕቆብም ወደ አባቱ ወደ ይስሐቅ ቀረበ፤ ዳሰሰውም፤ እንዲህም አለው፥ “ይህ ድምፅ የያዕቆብ ድምፅ ነው፥ እጆች ግን የዔሳው እጆች ናቸው” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያዕቆብም ወደ አባቱ ወደ ይስሕቅ ቀረበ፤ ዳሰሰውም እንዲህም ይህ ድምፅ የያዕቆብም ድምፅ ነው እጆች ግን የዔሳው እጆች ናቸው አለው። |
በሚካ ቤት አጠገብ እንደ ደረሱም የወጣቱን ሌዋዊ ድምፅ ዐወቁ፤ ስለዚህ ወደዚያ ጐራ ብለው፥ “ወደዚህ ያመጣህ ማን ነው? እዚህ ምን ትሠራለህ? የመጣኸውስ ለምንድን ነው?”። ሲሉ ጠየቁት።